Connect with us

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት በሠራተኞቹ ተተቸ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት በሠራተኞቹ ተተቸ
Photo: Facebook

ዜና

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት በሠራተኞቹ ተተቸ

የታላቁ ህዳሴ ግደብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት የተቋቋመው የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎን በማሳደግና በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ከአጎራባች አገሮች ጋር ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመፍጠርና መልካም ገጽታን ለመላበስ በማሰብ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም በቀድሞው የኢህዴግ ጉምቱ ባለስልጣን በአቶ በረከት ስምኦን የተቋቋመ ነው፡፡ በመቀጠልም የዛሬው የዴሞክራሲ ግንባታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ መርተውታል፡፡ ይሁንና ይህ ተቋም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት እስትራቴጂክ ዶክመንት ሳያዘጋጅ ፣ የተጠና ተቋማዊ አደረጃጀት ሳይመሰረት ፣ ሁለት ዘርፎችን ፣ አምስት ዳይሬክቶሬቶችንና ኮሮፖሬት የስራ ክፍሎች በመፍጠር አንድና ሁለት ባለሙያ በመያዝ ተልዕኮንና ሚናውን በአግባቡ ሳይለይ የመኪና ፣ ነዳጅ ፣ የወንበር አበል ..ወዘተ ወጭዎችን በማውጣት የህዝብና የመንግሥት ሀብትን በማባከን ላይ ይገኛል፡፡

ከተሰጠው ሃላፊነት ውጭ በህግ ሳይደገፍ የተለያዩ የውስጥ ሀብት ማስገኛ ሥራዎች ይሰራል ፣ ከህዝብ ተለያዩ ሥራዎች በአይነትም ሆነ በገንዘብ ሀብቶች ይሰበስባል፡፡ ነገር ግን በምን ዓይነት የሂሳብ አያያዝ እንደሚሰራ ፣ ከተለያዩ አካላት በገንዘብ እና በአይነት የተሰጡ ድጋፎች እንዴት እንደሚሰበሰቡ የህግ ማዕቀፍ ሳያዘጋጅ ፣ የገቢና የወጪ አሰራር ሳይዘረጋ ፣ በግብታዊነትና ምንም አይነት ጥናት ሳያካሂድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን ከግምት ሳያስገባ የተጀመሩ እንደ ዲያስፖራ ሎተሪ አይነት ኪሳራ ያስከተሉ ተግባራትን በማከናወን ፣ በአይነት ከህዝብ የተሰበሰቡ ንብረቶች በወቅቱ ተሰብስበው ገቢ ባለመደረጋቸው ከፍተኛ ብልሽትና ብክነት የተዳረጉበት፣ የቦንድ መረጃዎች በአግባቡ ያልተሰነደበትና ከህዝብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በአግባቡ መፍታት ያልተቻለበት ፣ በህዝብ የተለገሱ እቃዎች ለረጅም ጊዜ ተከዝነው ለብልና ለመበላሽት የተዳረጉበት (የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ፣ አልባሳት ፣ መኪናን ይጨምራል) ፣ በወቅቱ ያልተሰበሰብን ገንዘብ ለሚዲያ መረጃ በመስጠት መንግስትና ህዝብን ማሳሳትና ህዝቡ ሊያደረግ የሚገባውን ድጋፍ ማቀዛቀዝ ፣ ለረጅም አመት የቆዩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከግል አልሚዎች ለግደቡ ግንባታ የተለገሱ ቤቶች ገቢ ያለሆኑበት ፣ አንዳንዶችም ለእድሳት ወጪ ወጥቶባቸው ለተጨማሪ ኪሳራ የተዳረጉ መሆናቸው ፣ በውስጥ ትስስር እና ማንነት ላይ ያተኮረ ቅጥር ማካሄድ (አማካሪ እና ዳይሬክተር በማድረግ) ፣ የክልል ተዋረድ ጽ/ቤቶችን በአግባቡ ባለማደራጀት ደካማ አቋም እንዲኖራቸው በማድረግ ወጥነት ያለው ፣ አዳጊና ልምድ ሊሆን የሚችል ተቋም ባለማደራጀት ፣ ለግደቡ የተለገሱ ሀብቶችን ለግል ፍላጎት በማዋል (RVA-መኪና ለወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ተጨማሪ በማድረግ) ፣ የግድቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ያልተረጋገጠ የ3ዲ ፕሮጀክት ለመተግበርና ለዚሁ ስራ የሚውል ድሮን እና ካሜራዎችን በመግዛት አላስፈላጊ ወጪና በቅጡ ያልተጠና ስራ ለመስራት በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ግድፈቶች በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪ ተቋሙ ከሚጠበቅበት ሃላፊነትና አገር ከሚጠብቅበት ተልኮ ይልቅ ለተወሰኑ ሰዎች የግል ፍላጎትና ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ተወዳዳሪ ያልሆኑ ፣ እድሜያቸው የገፋና ጡረታ ላይ ያሉ ግለሰቦችን በማሰራት ለእነሱ ታማኝና ተላላኪ የሆኑ ግለሰቦችን በአመራርም ይሁን በባለሙያ ያስቀምጣሉ፡፡ የአመራር ቡደን በመፍጠር የሠራተኛን ጥያቄ ከመስማትና ተቋሙን ከማሻሻል ይልቅ የተለያዩ መግፊያ መንገዶችን በመፈለግ ጥቂት አቅም ያላቸውን ሰራተኞችን ያባርራሉ ፣ የማይለቁትን ደግሞ ኮንትራታቸውን ምክንያት በመፈለግ በማቋረጥ ዜጎችን ያንገላታሉ፡፡ በአጠቃላይ ተቋሙ አንደተቋም የሚመራ ሳይሆን በሶስትና አራት ግለሰቦች ፍላጎት የሚዘወር ፣ ለለውጥ እራሱን ያላዘጋጀ ፣ ቀጣይም ለአገር ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎችን የማይሰራ ፣ ያለውንም ለውጥ የማይቀበሉ ግለሰቦች ስብስብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዋናው ዳይሬክተር ይልቅ ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ፍቅረተ ታምር ወንድምአገኝ ነገሮችን በማወሳሰብ ፣ ኔትወርክ በመዘርጋት ፣ሀብት በማባከን ፣ የማይመለከታቸው ውስጥ በመግባት ሰራተኛን ማባረር እና ለሁለንተናዊ ተቋማዊ ውድቀት ተጠያቂ ሲሆኑ ዋና ዳይሬክተሯ ብዙውን ጊዜ በድርጅታዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩና መቀሌ የሚመላለሱ በመሆናቸው ፣ የተነገራቸውን በመቀበልና ለአመራሩ በመወገን ተቋሙ ብቃት ባለው ሰው እንዳይመራ በማድረግ ከፍተኛ ክፍተት እንዲኖር ፈቅደዋል፡፡

ይሁንና ይህ አሰራር አንዲሻሻልና ለውጥ አንዲመጣ በአቅምም በልምድ ብቃት ያላቸው ጥያቄ የሚያቀርቡ ሰራተኞችን ኢ-ፍታሃዊ በሆነ መንገድ ከስራ ገፍቶ ማስወጣት ፣ ኮንትራት ማቋረጥ እና ማገድ እንዲሁም ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀምን ግቢው ውስጥ ባለው የፌድራል ፖሊስ እዝ በማስፈራራት ከፍተኛ ኢ-ሰባዊ ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡

በመሆኑም የሚመለከተው አካል ሁሉ እንደየ ድርሻውና ኃላፊነቱ በዚህ ተቋም ውስጥ ያለውን ችግር መቅረፍና ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ስላለበት ቅሬታችንን ይመለከተዋል ለምንለው መንግሥታዊ የሆነ አካል በሙሉ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

(ይህ አስተያየት የጸሐፊዎቹን እንጂ የድሬቲዩብ ኤዲቶሪያል አቋም አያሳይም፡፡በጹሑፉ ላይ አስተያየት መስጠት ከፈለጉ editor@diretube.com ይጠቀሙ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top