Connect with us

124ኛው የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበሯል

124ኛው የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበሯል

ባህልና ታሪክ

124ኛው የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበሯል

አድዋ ከተማ በብሔራዊ ደረጃ አዲስ አበባ ደግሞ በህዝብ ሱናሚ አክብረውታል፡፡ ጎንደር ኮምቦልቻ ባህር ዳር በድምቀት ከተከበረባቸው አካባቢዎች መካከል ይገኙበታል፡፡

124ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሯል፡፡ በዓሉ በብሔራዊ ደረጃ በአድዋ ከተማ በሶሎዳ ተራራ ግርጌ የተከበረ ሲሆን የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረጽዮን እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ታድመውበታል፡፡


በአዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የተከበረው በዓል ከፍተኛ የህዝብ ሱናሚ የታየበት አዲስ አበባ በሁሉም አቅጣጫ ደምቃ የዋለችበት በዓል ነበር፡፡ የአዲስ አበባው በዓል ከዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ በእግር ጉዞ የተደረገበት ደማቅ ኩነት ሲሆን በዓሉ በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ከተማ፣ በባህር ዳርና ጎንደር በድምቀት ተከብሯል፡፡ በየአካባቢው የነበረውን አከባበር ከስፍራው ባገኘናቸው ፎቶዎች ከዚህ መረጃ ጋር አካፍለናችኋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top