Connect with us

እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን

እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን፤
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን

እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን፤
በዓለም ላይ ብዙ ሴቶች ስማቸውን ከፍ አድርገዋል፤ እርስዎ ግን ከፍ ያደረጉት የሀገር ስም የአህጉር መንፈስ ነው፡፡
***
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የአድዋ ትረካዎቹን ቀጥሏል፡፡ አድዋ ሲነሳ የማይነጠሉት የንጉሠ ነገሥቱ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ የድሉ አንድ ምልክት ናቸው፡፡ እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን ሲል ሄኖክ ስዩም እንዲህ ይዘክራቸዋል፡፡ l ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

እቴጌ ሆይ እንወድዎታለን፤ እርስዎን ያፈራች አህጉር ምነኛ እድለኛ ናት፡፡

እቴጌያችን መለኛ ናቸው የንጉሥ ሚስት የሀገር ክብር፤ አድዋን ባሰብሁ ጊዜ እንደምን እቴጌን መርሳት ይቻላል፡፡ ድሉ ክብር ሲሆን እሳቸው ዘውዱ ናቸው፡፡ ከዚያ ውብ የጥቁር ህዝቦች ድል ጀርባ ጥቁር ንግሥት ከሀገሬ የሚበልጥ የለም ማለቷን ከእኛ ይልቅ አለም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

ጦርነትን ጦርነት ስለሆነ እንጂ ሴት ስለሆነች የማትፈራዋ ንጉሥ በሌላው ዓለም ዘንድ ትርጉሟ ብዙ ነው፡፡ እኛ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እንላታለን፡፡ በጨለመ ሰዓት የበራች፤ በሚያስፈራሩት ፊት የደፈረች፣ በሚዋጉት ግንባር ድል ያደረገች፡፡ ጠሐይም ሐይቱም፤
ጣይቱ የእኛ ጸሐይ ናት፡፡ ደብረ ታቦር የሰረቀች፣ በየዳ ደመና የገፈፈች፣ ደብረ መዊ የናጸባረቀች፣ አንኮበር ጉም ያበረረች፣ ዓዲስ ዓለም አዲስ ትውልድ የሞቃት፣ እንጦጦ ደምቃ የታየች፣ አድዋ ለዓለም ያበራች፤ ጣይቱ የእኛ ጸሐይ ናት፡፡

በዓለም ብዙ ሴት እናውቃለን በውበት ዓለምን ስለማሸነፍ የሚደክሙ የእኛ ጸሐይ ግን በዓለም ካሉት ሴቶች አብልጠን ልዩ ናት እምንለው በፍትሕ ዓለምን የረታች ጦር መርታ የድል ጽዋን የጠጣች የእናቶቿ የእነ ማክዳ ልጅ፣ የነ ህንደኬ ልጅ፣ የነ ሰብለወንጌል ልጅ፣ የነ ምንትዋብ ልጅ የእኛ እናት ጣይቱ፤

በዓለም ላይ ብዙ ሴቶች ስማቸውን ከፍ አድርገዋል፡፡ ራሳቸውን አክብረዋል፡፡ የእኛ ጣይቱ ግን የእኛን ስም ከፍ አድርጋለች፡፡ የአህጉራችንን መንፈስ አናኝታለች፡፡ በሚያስከብር ስራ አስከብራናለች፡፡

ንግሥታችን ስንል አብረን የምንጠራው ስልጣኔ ድልና ክብር ነው፡፡ አንቺ የሀበሻ እናቶች ምልክት ነሽ፣ አንቺ የጥቁር ሁሉ ዓርማ ነሽ፤ አንቺ ከትልቁ ድላችን ጋር ስምሽን የምናነሳው ማስታወሻችን ነሽ፡፡ እናም እቴጌ ሆይ እንወድሻለን እንላታለን፤
እንዲህ የምንወዳት ንግሥት ልዩ ናት፡፡

ምጣዷ ላይ ነጻነትን የምትጋግር፣ ሌማቷ ላይ ድልን ለሀገር ማዕድ የምታቀርብ፣ ሽክፋዋ በአሸናፊነት የተሞላ፣ እኛ መገዛትን የምንጠየፍ ጣይቱን ጸሐያችን እንላታለን፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top