Connect with us

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለሆኑ መኖሪያ ቤቶች የ69 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

በኢንተርፕራይዝ ደረጃ ደግሞ የ65 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ መደረጉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ለቨርችዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (ቪፒኤን) ተጠቃሚዎችም እንዲሁ የ72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።

ታሪፍ ላይ ከተደረገው ማሻሻያ በተጨማሪ የኢንተርኔት ፍጥነቱ ላይም ማሻሻያ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ለማሻሻያ ስራው ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ውጪ መደረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።

የተደረገው ማሻሻያ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያግዛል ተብሏል።

#EBC

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top