Connect with us

“በእጅጉ አዝኛለሁ” ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

"በእጅጉ አዝኛለሁ" ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
Photo: Facebook

ፓለቲካ

“በእጅጉ አዝኛለሁ” ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

አሁን በታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተደረገ ያለው ድርድር አሳዛኝ ነው፣ ፈፅሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መሄድ አልነበረበትም፣ ይህ ደግሞ የአመራር ችግር ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው።” ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዶክተር ደብረጽዮን የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በግል የሚሰማቸውን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ግድቡ ከጅማሬው አንስቶ በ2010 ዓ.ም. ወደ ክልሉ በአመራርነት እስከሄዱበት ድረስ ያለውን በማውሳት፣ አሁን ያለበት ሁኔታ በጣም እንዳሳዘናቸው ጠቁመዋል፡፡

‹‹በግሌ እጅግ አዝኛለሁ፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ መንግሥት አሁን እያደረገ ባለው ነገር የግድቡን ሥራ ወደ ኋላ ጎትቶታል ይላሉ፡፡ ግድቡን በራስ አቅም በመገንባት የኃይል ፍላጎትን ለማሟላት እግረ መንገዱን የኃይል ምህንድስና ኢንዱስትሪዎች ለማቋቋም ይረዳ ነበር ብለው፣ ይህ ዕቅድ በአመራር ስህተት ተጨናግፏል ሲሉ አክለዋል፡፡ ‹‹በተለይ ሜቴክ የአስተዳደር ጉድለቶች እንደነበሩበት በግል የማምን ቢሆንም፣ ችግሩን አስተካክሎ መሄድ ሲቻል ሙሉ በሙሉ ከሥራው ውጪ እንዲሆን መደረጉ ትክክል አልነበረም፡፡

ግድቡን በአንድ ዓመት ውስጥ አጠናቀን የመጀመርያ ምዕራፍ ኃይል ማመንጨት ይጀምር ነበር፤›› ብለዋል፡፡ ከምንም በላይ የሚያሳዝነው ከአምስት ዓመት በላይ በዚያ በረሃ የነበሩ ወጣት ልጆች እንዲበተኑ መደረጉ እንደ አገር ትልቅ ኪሳራ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

‹‹በግድቡ ግንባታ ሜቴክ በነበረው ድርሻ ሙሉ ለሙሉ ጥሩ መሐንዲሶች ማፍራት ችለን ነበር፡፡ ለወደፊትም በራሳችን አቅም ለመገንባት የሚችሉ መሐንዲሶችን እናወጣ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ዛሬ ተጨናፍጓል፡፡ በአጭር ጊዜ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው መሐንዲሶችን እያፈራንና በውጭ አገር ባለሙያዎች ሳይቀር ለመወዳደር ይበቁ ነበር፡፡ ዛሬ እነዚህን ወጣቶች ሜዳ ላይ ቢበተኑ የአገሪቱን ህልም ማጨንገፍ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አሁን እየተደረገ ያለው ድርድርም አሳዛኝ ነው ብዋል፡፡ ‹‹ፈፅሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መሄደ አልነበረበትም፡፡ ይህ ደግሞ የአመራር ችግር ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹እኔ ወደ ክልል እስከሄድኩበት ዕለት ድረስ ግድቡ 63 በመቶ ደርሶ ነበር፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥም ያልቅ ነበር፡፡ ያኔ መቀሌ ከመጣሁ በኋላ ኢንጂነር ስመኘው መጥቶ ተወያይተን ነበር፡፡
እንድታግዘን ብሎኝ ነበር፡፡ እኔም ፍላጎቱ ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ግድቡ እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ያን ያህል ድርድር አያስፈልግም ነበር፡፡ የመደራደር አቅማችንም ትልቅ ነበር፡፡
የሰሞኑ ድርድር ግን የመደራደር አቅማችንን ወደ ኋላ የጎተተ ነው፡፡ ለምሳሌ ሱዳን በስንት ትግል በእጃችን አስገብተን አቅማችን ፈርጥሞ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ጭራሽ ሱዳንንም አጥተናታል፤›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ለምሳሌ በቅርቡ አይ ኤም ኤፍ ብድር ሲሰጥ በድርድሩ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር አገርን ተጋላጭ አድርጓል ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ‹‹ይህ ደግሞ የፖሊሲ ዓቅማችንንም ሊያሳጣን ይችላል፤›› ብለዋል፡፡

(ምንጭ :- የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top