Connect with us

የጋርዱላ ምድር ባህላዊና ኪነጥበባዊ እምቅ ፀጋ የታየበት ዘጋቢ ፊልም ለዕይታ በቃ

Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

የጋርዱላ ምድር ባህላዊና ኪነጥበባዊ እምቅ ፀጋ የታየበት ዘጋቢ ፊልም ለዕይታ በቃ

ፊልሙ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ፣ ተፈጥሯዊ ገፅታና ባህላዊ የሙዚቃና የጭፈራ ሀብቶችን የዳሰሰ ሲሆን ሰውኛ ፊልም ፕሮዳክሽን አዘጋጅቶ ክብረ አድዋ በተሰኘው ዓመታዊ የአድዋ በዓል መክፈቻ ሥነስርዓት ላይ ለዕይታ አብቅቶታል።

በበዓሉ መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳውና የባህል ዘርፍ ዴኤታዋ ወ/ሮ ብዙነሽን ጨምሮ በርካታ ታዳሚዎች ቸገኝተው ፊልሙንና ሌሎች ኪነጥበባዊ ክዋኔዎችን ተመልክተዋል።

በጋርዱላ ምድር በተለይም በገጠራማው አካባቢ ስላለው ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች አከዋወን እና እንደምታ የዳሰሰው ዘጋቢ ፊልሙ በአራቱ የአካባቢው ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከወኑ ባህላዊ ጭፈራዎችን በመጠኑ በመዳሰስ ዘገባ ቀርቦበታል።

በብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ በተዘጋጀው በዚህ መርሐ ግብር ላይ ከ560 ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዘው ከአካባቢው የመጡት የክራርና የማይራ ተጫዋቾች ታዳሚውን ያስደነቀ ክዋኔ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የጋርዱላ ተወላጅ ምሁራንም በሥነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የብዝሃ ባህል አምባ እና የታሪክ ማህደር የሆነችው ጋርዱላ ዘጋቢ ፊልሙ ያላሳያቸው የበርካታ ታሪካዊ ሀብቶች ባለፀጋ መሆኗንና በአድዋ ድል በዓል መክፈቻ ላይ እንደመቅረቡ የአድዋ ድልና የጋርዱላን ሚና የሚያሳዩ የአካባቢው ታሪኮች በፊልሙ መካተት ቢችሉ ተያያዥነት ሊኖረው እንደሚችልም የሚያውቋት ምሁራንና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በአድዋ ጦርነት ወቅት በ1888 ዓ.ም ከፊታውራሪዎችና ደጃዝማቾች በተጨማሪ ቁጥሩ ከፍ ያለ ሠራዊት ከጋርዱላ መዝመቱ ይነገራል። ከሠራዊቱ ጋር የዘመቱት ሁለቱ ታቦታት የአዲስ አበባው አራዳ ጊዮርጊስና የጋርዱላ ጊዮርጊስ መሆናቸው ልብ ይሏል።

በካሣሁን አሰፋ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top