Connect with us

ስዬ አብርሀ አሁን ለተፈጠረው አገራዊ ቀውስ ህወሓትንም ተጠያቂ አደረጉ

Photo: Facebook

ፓለቲካ

ስዬ አብርሀ አሁን ለተፈጠረው አገራዊ ቀውስ ህወሓትንም ተጠያቂ አደረጉ

የቀድሞ የህወሓት ታጋይ እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሰዬ አብርሀ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው አለመረጋጋትና ቀውስ ህወሓት አስተዋጽኦ እንዳለው ተናገሩ፡፡

አቶ ስዬ ከትግራይ ሚዲያ ሐውስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳስታወቁት አሁን የሚታየው አገራዊ ችግር የፈጠረው አዲስአበባ የተቀመጠው ፓርቲ ብቻ አይደለም ካሉ በኋላ ህወሓት ቀደም ሲል የፌደራል መንግሥቱ ሥልጣን በእጁ እያለ ነገሮችን እንዴት እናስተካክል ብሎ ኃላፊነት ወስዶ ቢንቀሳቀስ ኖሮ ዛሬ የሚታዩ ችግሮች ውስጥ ባልገባን ነበር ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት በሁለቱም ወገኖች በኩል የሚታየው ጣት መቀሳሰር ለማንም እንደማይጠቅም የጠቆሙት አቶ ስዬ ችግሮችን ቆም ብሎ በጋራ ለመፍታት መንቀሳቀስ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የትግራይ በፌዴራል መንግሥቱ ተገልላለች፣ ራስዋን የቻለች አገር ልትሆን ይገባል የሚሉ ጥያቄዎች ስለመኖራቸው ተጠይቀው “አገር ትሁን ወይንስ አትሁን ወደሚለው የዘመኑ ወጣቶች ፖለቲካ ውስጥ መግባት አልፈልግም ካሉ በሃላ ከዚያ በፊት መመለስ የሚገባቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ ብለዋል፡፡ በትግል የተከበረ ማንነታችን፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን የሚወስድብን አይኖርም ያሉት አቶ ስዬ ከዚያ በፊት ግን ትግራይን ራስን ወደመቻል አድርሰነዋል ወይ፣ ዴሞክራሲ፣ ጠንካራ ተቋማት ገንብተናል ወይ፣በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ…ትግራይ ውስጥ መስራት ያለብንን ሰርተናል ወይ፣ ማንም ሰው በተግባሩ የሚለካበት፣ የሁላችንም ሀሳብ፤ ገበታ ላይ ቀርቦ ተሳስቦ የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረጽ የሚያስችል ሁኔታ ተፈጥሮአል ወይ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

አቶ ስዬ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት የህወሓትን ምስረታ 45 ዓመት በዓል ለመታደም መቀለ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top