Connect with us

ህወሓት በምርጫ ቦርድ እንደአዲስ ተመዘገበ

ህወሓት በምርጫ ቦርድ እንደአዲስ ተመዘገበ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ህወሓት በምርጫ ቦርድ እንደአዲስ ተመዘገበ

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ውህደት ራሱን ካገለለ በኋላ በምርጫ ቦርድ እንደአዲስ ተመዝግቦ እውቅና ማግኘቱ ተሰማ፡፡

ህወሓት በፋዊ ድረገጹ ከብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና አሠራር ጋር አብሬ አልቀጥልም ማለቱን በማስታወስ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ሥነ-ምግባር ለመደንገግ በወጣው በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት እንደ አዲስ መመዝገቡን ጠቅሷል፡፡

ህወሓት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ምርጫ ቦርድ በሕጉ መሠረት ተገቢውን ሁሉ ማሟላቱን አረጋግጦ የካቲት 4 ቀን 2012 እውቅና እንደሰጠው ይፋ አድርጓል፡፡

ህወሓት የቀድሞ ኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ውህደት ጉባዔው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አልተከናወነም በሚል በይፋ ውህደቱን በመንቀፍ ራሱን ማግለሉ የሚታወስ ነው፡፡

[ቢቢሲ፣ የህወሓት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ]

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top