Connect with us

አቦል ጀባ ብዬ ቡናዋን ብቀምሰው….

አቦል ጀባ ብዬ ቡናዋን ብቀምሰው….
Photo: Facebook

ፓለቲካ

አቦል ጀባ ብዬ ቡናዋን ብቀምሰው….

አቦል ጀባ ብዬ ቡናዋን ብቀምሰው….
ድሮም ጅማ የፍቅር ሀገር ናት
ጅማ የመደመሩ አስኳል
******
(ከስናፍቅሽ አዲስ)

ጅማ አደባባይ ወጣች፤ ሆ ብላ የታየችው ጥላቻን አንግባ አይደለም፡፡ ሆ ብላ የወጣችው ዘር ቆጥራ አይደለም፡፡ ጅማን ጎዳና ላይ ያወጣት እየታየ የመጣው እየሆነ ያለው ጠቅላዮን የማሳደድ ዘመቻ ነው፡፡

ዶክተር አብይ ብዙ አካባቢዎች አድልዎ ኦሮሞ ተደርገው ይቆጠራሉ፤ ከመቆጠር ባለፈ የቀደመ የድጋፍ ፍቅራቸውን የነፈጓቸውም ብዙ ናቸው፡፡ የነ ጃዋር ቡድን ጠቅላዩን ከኦሮሞ ለመነጠል ደግሞ ያለ እረፍት እየሰራ ነው፡፡ ኦሮሞን እና ዶክተር አብይን መነጠል ይቻላል አይቻልም የሚለው ምላሽ ምርጫና የምርጫ ውጤትን የሚጠብቅ ቢሆንም ጅማ ግን ምልክት ሰጥታለች፡፡

ጅማ የፍቅር ሀገር ናት፤ ጅማ ራሷን የምትገልጸው በአብሮ መኖር ሲሆን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የአክራሪ ብሔርተኞች ዓይን አርፎባት ነበር፡፡ አክራሪዎች ሰላሟን ገፈው ትከሻዋን ሊያቀሉ ሞክረዋል፡፡ አርሶና ነግዶ የሚኖር ማህበረሰብ አብሮነትና ሰላም ምትክ የለሽ ጥቅሙ እንደሆነ እየታወቀ ጅማን ክፉ ምድር ለማስባል ብዙ ተሞክሮም ነበር ሁሉን ያከሸፈችው ጅማ ዛሬ ዳግም የመደመሩ አስኳል መሆኗን አሳይታለች፡፡

የጅማ ሰልፍ ምክንያቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መደገፍ ብቻ አይደለም፤ እንደ እኔ መልእክትም ነው፡፡ የትም ኦሮሚያ መበጥበጥ ይቻል ይሆናል ጅማ ግን ይሄ የህልም ቅዥት ነው የሚል መልእክት ነው፡፡ ማን ያውቃል የጅማን ወኔ ሸዋ አንስቶት እናይ ይሆናል፡፡

ኦሮሞው ባህሉም እምነቱም የማይፈቅድለትን በብሔርተኝነት ስም እንዲያደርግ የተገደደበት የነጻነት አፈና ላይ ነው፡፡ ስቃዩን ያያል፤ ዛሬም ሰርቶ መግባት ዛሬም ለኢንቨትመንት የተመቸ አከባባቢ ነው መባል ብርቅ እየሆነበት ነው፡፡ ቁጥር የማይገቡ ሰዎች እጣ ፈንታውን ወስነውለታል፡፡ መጠመቁን እንኳን ብሔሩን የመቀየር ያክል እንደሆነ በአደባባይ ነግረውታል፡፡

አቦል ጀባ ብዬ ቡናዋን ብቀምሰው….

ጅማ አደባባይ ወጣች፤ ሆ ብላ የታየችው ጥላቻን አንግባ አይደለም፡፡ ሆ ብላ የወጣችው ዘር ቆጥራ አይደለም፡፡ ጅማን ጎዳና ላይ ያወጣት እየታየ የመጣው እየሆነ ያለው ጠቅላዮን የማሳደድ ዘመቻ ነው፡፡

ጅማ የንቃት ፊሽካውን ነፍታዋለች፡፡ ጉዳዩ አብይን የኛ ነው ከማለት ያለፈ ነው፡፡ ዶክተር አብይ ህዝብ አለው ማለት እኛ ህዝብ ነን መንጋ አይደለንምና የምናደርገውን ስለምናውቅ የጃዋር ጥሪ አያስፈልገንም የሚል ነው፡፡ የጃዋር ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ነገ ከነገ ወዲያ እናየዋለን፡፡

እንዲህ አይነቱ ጥሪ ነገ በሰላሌ በአምቦ በወሊሶ በገላን የሚደገም እንደሚሆን ግን እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም የወንድሞቻችንን ልብ እናውቀዋለንና፤ ፍቅራቸውን እንረዳለንና፤ አክራሪውን ለመረዳት ከዚህ በላይ የሞኝ ርቀት እንደማይሄዱ እንገነዘባለንና፤ ብራቮ ጅማ፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top