Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ ጉብኝት ያደርጋሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ ጉብኝት ያደርጋሉ
Photo: Facebook

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ ጉብኝት ያደርጋሉ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2012 ዓም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሚያደርጉት ጉብኝት የተቋቋመው አብይ ኮመቴ ዝግጁትን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓም በዱባይ ከተማ ሸባብ አልአህሊ ክለብ በአልመክቱም ስታዲያም የሙሉ ቀን ዝግጅት ላይ በመገኘት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በመካከለኛው ምስራቅ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መልእክት ያስተላልፋሉ።

ይህንኑ ዝግጅት ለማስተባበር ከህብረተሰብ አደረጃጀቶች ከሃይማኖት አባቶችና ከልማት ማህበራት የተውጣጣ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።

በተለይ አርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓም ህብረተሰቡ ከሰባቱም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዛቶች ሁሉም በነቂስ ወጥቶ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርን እንዲቀበልና እንዲገናኝ ለማድረግ እየተከናወኑ ስላሉ እንቅስቃሴዎች የቅስቀሳ፣ የመስተንግዶ እነ የሎጀስቲክ ስራዎች በተመለከተ የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና በዱባይ ከኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማሪያም ጋር ትናንት የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top