Connect with us

1 ሺህ 143 የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተዋል

1 ሺህ 143 የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተዋል
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

1 ሺህ 143 የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተዋል

በኩባንያዎቹ 192 ሺህ ዜጎች ተቀጥረዋል

በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፍ የተሰማሩ የቻይናውያን ፕሮጀክቶች ቁጥራቸው 1ሺህ 143 መድረሱን እና በፕሮጀክቶቹ ውስጥ ለ192 ሺህ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድሎችን መፍጠራቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለፀ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኃይሉ እንደገለጹት፤ ቻይና ወደኢትዮጵያ ከሚመጡ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ካላቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች። በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 143 የቻይናውያን ፕሮጀክቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ሲሆን፤ አብዛኞቹ የቻይና ኩባንያዎች ኢንቨስትመንት በማምረቻ ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ነው።

እንደ አቶ መኮንን ገለጻ፤ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱ የቻይና ኩባንያዎች መካከል 621ዱ ፕሮጀክቶች በስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ 144ቱ ደግሞ በቅርቡ ወደስራ የሚገቡ እና በትግበራ ደረጃ የሚገኙ እንዲሁም 378ቱ ደግሞ በቅድመ ትግበራ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው። ስራ በጀመሩት እና ወደማምረት በተሸጋገሩ 621 ፕሮጀክቶች ውስጥም ለ130ሺ 673 ቋሚ እና ለ61ሺ 854 ጊዜያዊ የስራ እድሎች ተፈጥረዋል። በመሆኑም በቀጣይ ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል እድል ተፈጥሯል።

የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን እንደተናገሩት ፤ በቻይናውያን ከሚመሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል 867ቱ በማምረቻ ዘርፍ ላይ የተሰ ማሩ እና የተለያዩ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማምረቻ ኩባንያዎች ናቸው። ሌሎች 130 ኢንቨስትመንቶች ደግሞ በግንባታው ዘርፍ ተሰማርተዋል። በመሳሪያዎች ኪራይ እና ማማከር ስራ የተሰማሩ ደግሞ 95 ናቸው። በተጨማሪ ደግሞ በሆቴልና ሎጅ ዘርፍ 28 ፣ በግብርናው መስክ 10 እና ኮሙዩኒኬሽንና ትራንስፖርት እንዲሁም በአስጎብኚነት ዘርፎች ደግሞ 13 ኩባንያዎች ተሰማርተዋል።

እንደ አቶ መኮንን ከሆነ፤ ከቻይና የሚመጣው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በየዓመቱ እያደገ ይገኛል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በመቶዎች ብቻ የነበረው ኢንቨስትመንት አሁን ላይ በሺዎች ደረጃ ደርሷል። በተጨማሪም ቻይናውያን ኩባንያዎች በእራሳቸው አቅም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየገነቡ ናቸው ። በአሁኑ ወቅትም በአረርቲ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በቻይና ኩባንያ አማካኝነት እየተገነባ ይገኛል። ይህም ቻይናውያን በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ላይ የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ ማሳያ ነው።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን ከሁለት ወራት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፤ በየጊዜው ግዙፍ የቻይና ኩባንያዎች ወደኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት እያሳዩ ነው። ለአብነት በዓለም ትልቁ የሆነ የካልሲ አምራች ኩባንያ ወደኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት እንዳለው ገልጾ ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ጀምሯል። ይህም ለኢትዮጵያውያን ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር ያግዛል።

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥር 30/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top