Connect with us

የሁለት ሀገር ፓስፖርት ይዞ ሀገር መበጥበጥ ሊቆም ይገባል ተባለ

የሁለት ሀገር ፓስፖርት ይዞ ሀገር መበጥበጥ ሊቆም ይገባል ተባለ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የሁለት ሀገር ፓስፖርት ይዞ ሀገር መበጥበጥ ሊቆም ይገባል ተባለ

ፖለቲከኛም ይሁን አክቲቪስት የሁለት ሀገር ፓስፖርት ይዞ ሀገር መበጥበጡን ሊያቆም ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር አሳሰበ።

ማህበሩ የፊታችን የካቲት 3/2012 ዓ.ም የሚካሄደውን የሰላም ኮንፍረንስ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጠበት ወቅት በውጪ ሀገር ፓስፖርት እየኖሩ ሀገር መበጥበጥ አይቻልም ብሏል።

የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ እንድሪስ መሀመድ በውጪ ሀገር እየኖሩ የሀገር ውስጥ ሰላምን ማሳጣት መቆም እንዳለበት አሳስበው በአገሪቷ ለሚታዩ አንዳንድ አላስፈላጊ ግጭቶች ምክንያት የሆኑ ዳያስፖራዎች ለህግ መቅረብ አለባቸውም ብለዋል።

ሰብሳቢው ሁሉም ዜጋም ለሀገር ሰላም የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡፡

የፊታችን የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በሚደረገው ኮንፍረንስ ላይም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ዳያስፖራው በሰላም ጉዳይ ላይ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሚደረግ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

መንግስት ለሚያደርገው ለእያንዳንዷም ሰላምን የማስከበር ስራ ማህበሩ ከጎኑ እንደሚሆንም በመድረኩ ተነግሯል፡፡

ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top