Connect with us

ኢሳይያስ አፈወርቂ ህወሓትን በጸረ ሠላም እንቅስቃሴ ከሰሱ

ኢሳይያስ አፈወርቂ ህወሓትን በጸረ ሠላም እንቅስቃሴ ከሰሱ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢሳይያስ አፈወርቂ ህወሓትን በጸረ ሠላም እንቅስቃሴ ከሰሱ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው በትላንትናው ዕለት ለኤርትራ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ በዚሁ መግለጫቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሠላም ስምምነት ወደፊት እንዳይራመድ ህወሓት መራሹ ቡድን ትልቅ እንቅፋት እየፈጠረ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሀገራቸውና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረውና ለአንድ ዓመት ተኩል የዘለቀው ግንኙነት ብዙ ሥራ የተከናወነበት ባይሆንም መልካም ጅምር እንደሆነ አመልክተዋል።

በሁለቱ ሀገሮች መካከል ለቆዩት ችግሮች በዋንኛነት ተጠያቂ ያደረጉት ህወሓት ሰሆን በቀታይ ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ ህወሓቶች ከውጭ ጣለቶች ጋር በመተባበር ችግሮችን እየፈጠሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጽያ እና ኤርትራ የሠላም ግንኙነት ለማደናቀፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ብሔረሰቦች ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ እየሰሩ ያሉት የህወሓት መሪዎች ናቸው ሲሉ ክስ አቅርበዋል፡፡

የህወሓት ሰዎች በዶ/ር ዐብይ አሕመድ እና በኢሳይያስ አፈወርቂ ተከበናል በማለት አዲስ ስልት ይዘው ብቅ ማለታቸውን ጠቁመው በአልጀርስ ስምምነት መሠረት ተገቢው የድንበር ማካለል እንዳይከናወን ሕወሓቶች በባድመ አካባቢ ለእርሻና ለመኖሪያ ቤቶች አዲስ ሰፈራ በማከናወን እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top