Connect with us

የኮሮና ቫይረስን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው ሐኪም የቫይረሱ ሰለባ ሆኖ ሞተ

የኮሮና ቫይረስን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው ሐኪም የቫይረሱ ሰለባ ሆኖ ሞተ
Photo: Facebook

ጤና

የኮሮና ቫይረስን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው ሐኪም የቫይረሱ ሰለባ ሆኖ ሞተ

ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ በውሃን ማእካላዊ ሆስፒታል ስራውን ሲያከናውን በቫይረሱ እንደተያዘ ታውቋል።

የዶክተር ሊ ሞት ለቻይናውያን የልብ ስብራትን፤ ለሀገሪቱ መሪዎች ደግሞ የፖለቲካ ኪሳራን አስከትሏል።

በታህሳስ ወር የኮሮና ቫይረስ በዋናነት የተቀሰቀሰባት የውሃን ከተማ ባለስልጣናት ስለበሽታው መከሰት የሚያመላክቱ መረጃዎችን ለመሸፋፈን ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

የበሽታውን መከሰት በተመለከተ ለሰዎች በመንገር እንዲጠነቀቁ ሲመክር የነበረውን ይህን ሐኪም ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀውት ነበር።

የዶክተር ሊ ዌንሊያንግን ሞት ተከትሎ አሁን በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን እና ቁጣ ተቀስቅሷል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top