Connect with us

የሌሊት ፖሊሶችና የማይነጋላት ሀገር

የሌሊት ፖሊሶችና የማይነጋላት ሀገር

ህግና ስርዓት

የሌሊት ፖሊሶችና የማይነጋላት ሀገር

ልጅን ከጦር ሜዳ ያስቀሩታል፤ ከፖለቲካ ያርቁታል፤ ቤተስኪያን ከተገደለ ትምህርት ቤት ከታገተ ወዴት ያኖሩታል?
****
ከስናፍቅሽ አዲስ

ሌሊቱን ከሌባ ስንፈራ ከገዳይ ስንሰጋ የኖርን ህዝቦች ነን፡፡ ሌሊት ፖሊስን ከመፍራት አልፈን በሌሊት በፖሊስ የምንሞትበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የጉዳዩን ልክ ነው አይደለም ባይነት ሳይሆን ችግርን ለመፍታት የምንሄድበት መንገድ ትውልድ የሚያፍርበት ጸያፍ ተግባር ነው፡፡

ዛሬም የሌሊት ፖሊሶች ቤት ሰብረው ሰው ለመያዝ ከቋመጡ፣ ዛሬም ህገ ወጥን ለመከላከል ህገ ወጥ አመጣጥ ከመጡ፣ ዛሬም ጨለማውን እንደ ሌባ ፖሊስ ተሸሽጎ ህገ ወጥ ስራ ከሰራበት ለኢትዮጵያ የሚነጋላት መቼ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብስ?

በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “አዲስ አበባ ይሄን ያህል ሌባ አለ፤ ይሄን ያህል ፖሊስ አሰልጥነናል፤ በድምሩ የሌባው ቁጥር እንዲህ ደርሷል” አሉ ተብሎ ፖሊሱን ጨምሮ ከሌባው ቁጥር ጋር ደመሩት የተባለበት ወሬ እንዲህ ባለው ጊዜ ስንመለከተው እውን ይሆን? ያስብለናል፡፡

ቀደም ባለው ግዜ ልጅ እንዲያደግ ከጦር ሜዳ ማሸሽ ነበር መፍትሔው፤ ልጅን የሚሳጣ ሰላም ማጣትና ጦርነት ነበር፡፡ ከጦርነት የተረፈውን ትውልድ ደግሞ ፖለቲካ በላው፤ አባረርነው ያልነው ኢህአዴግ እንኳን ፖለቲካን ሸሽቶ ኑሮውን ማሸነፍ ከሚሻ ጋር ተጋጭቶ አያውቅም፡፡

አሁን ያለው አበሳ ያለ ቦታው ነው፡፡ ልጁን ትምህርት ቤት የላከ እሬሳ ይቀበላል፡፡ ትምህርት ቤት ከመላክ በላይ ሰላማዊ ቦታ ባይኖርም የጦር ሜዳን ያህል አልቅሶ መሸኘት ካልታደሉም ሬሳ ተቀብሎ አልቅሶ መቅበር ባህል ሆኗል፡፡ ልጅን ከትምህርት ቤት ውጪ የትስ መላክ ይቻላል? የትስ አስቀርቶ ልጅን ማትረፍ ይቻላል?

መቼም የወጣትነት እድሜን በእምነት ተቋማት እንደማሳለፍ መልካምና የሚመከር ነገር የለም፤ ቀላልና በውይይት መፈታት በሚችሉ ችግሮች ምክንያት በእምነት ተቋማት መሞት፣ ታቦት አጅቦ መገደል፣ ቤተስኪያን በር ላይ በጥይት መመታት፣ መስጂድ ደጃፍ መውደቅ አሳዛኝ ነው፡፡

ነገን ስናስብ ከትናንት እንደሚከፋ እርግጠኛ የምንሆነው ዛሬን ስናይ ነው፡፡ ዛሬ ሞት ቀላል፣ መኖር ብርቅ፣ ሰላም እንቁ ሆኗል፡፡ ታቦቱ በሰላም ገባ እና በሰላም ተሰግዶ ሶላት ተጠናቀቀ የሚለው ትልቅ ዜና ሆኗል፡፡ መንግስትን መጣል የሚሹ፣ መንግስት ሆነው መውደቅ የሚፈልጉም እኩል ጥፋትን የልማት ያህል ተወዳጅተዋል፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ዛሬም ኢትዮጵያዊት እናት እንደ ራሔል ስለ ልጆቿ ታለቅሳለች፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top