Connect with us

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳጋችው የኬንያ አቻቸውን ተቀብለው አነጋገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳጋችው የኬንያ አቻቸውን ተቀብለው አነጋገሩ

ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳጋችው የኬንያ አቻቸውን ተቀብለው አነጋገሩ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን በቅርቡ የተሾሙትን አምባሳደር ሪቼል አውር ኦማሞ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ መክረዋል።

 

አቶ ገዱ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ፣ በመተማመን ላይ የተመሰረተ፣ በመሪዎች መቀያየር የማይለዋወጥ እና በሁሉም ዘርፍ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

አቶ ገዱ በቀደሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለኬንያ ህዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል ከዚህ በፊት የተመሰረቱ ስምምነቶችን በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን በመለየት ግንኘነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበቸውም አቶ ገዱ አንስተዋል።

ሁለቱ አገራት ከዚህ በፊት የደረሱትን ”የልዩ ደረጃ ስምምነት” ተግባራዊ በማድረግ በኩል ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የሁለቱን አገራት ህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ለማሳካት መረባረብ አለባቸውም ብለዋል።

ሁለቱ አገራት ከሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በኢጋድ፣ በአፍሪካ ህብረት፣ በተመድ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚያደርጉትን ትብብር በየጊዜው እየፈተሹ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንዳለባቸውም አቶ ገዱ በዚህ ወቅት አንስተዋል።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪቼል አውር ኦማሞ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በየጊዜው እየተጠናከረ የመጣ እና በሁሉም ዘርፍ አመርቂ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው በቀጠናው ለታየው የሰላም እና ፀጥታ መሻሻል እውቅና የሰጠ በመሆኑ ኬንያ ልዩ ኩራት ይሰማታል፤ ሽልማቱ ለእርሷ እንደተሰጠ ትቆጥረዋለችም ብለዋል።

ሁለቱ አገራት በአሁኑ ስዓት በቀጠናው ያላቸውን ፖለቲካዊ ትብብር በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ይበልጥ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አምባሳደር ኦማሞ ገልጸዋል።

ሁለቱን አገራት በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።

የሁለቱ አገራት ህዝቦች ድንበር ከመጋራት ባለፈ ተመሳሳይ አኗኗር፣ ባህል እና ቋንቋ የሚጋሩ በመሆኑ የህዝቦችን ኑሮ ለማሻሻል የሚችሉ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመለየት በትብብር መስራት እንደሚገባም አምባሳደር ኦማሞ ተናግረዋል።

በተለይም በአሁኑ ሰዓት ምስራቅ አፍሪካን እያጠቃ ያለውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ እና ካለወቅቱ በሚጥል ዝናብ የሚከሰትን ጎርፍ ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ፕሮጀክት በመቅረጽ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አምባሳደር ኦማሞ አንስተዋል።

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top