Connect with us

የቀድሞ ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ በብሔራዊ ፓርኮች ዙሪያ ለሚሰሩት የበጎ አድራጎት ተግባር ብሔራዊ ፓርክ ጎበኙ

የቀድሞ የኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በብሔራዊ ፓርኮች ዙሪያ ለሚሰሩት የበጎ አድራጎት ተግባር የጨበራ ጩርጩራን ብሔራዊ ፓርክ ጎበኙ

ዜና

የቀድሞ ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ በብሔራዊ ፓርኮች ዙሪያ ለሚሰሩት የበጎ አድራጎት ተግባር ብሔራዊ ፓርክ ጎበኙ

ፕሮጀክታቸው የማዜ ብሔራዊ ፓርክንም ያካትታል።

የቀድሞው የ ኢ/ፌ/ዲ/ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከባለቤታቸው ጋር ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካኝነት ከሚሰሯቸው የልማት ስራዎች መካከል የብሔራዊ ፓርኮችና አካባቢያቸውን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የቱሪዝምና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ይገኙበታል።

አቶ ኃይለማርያም ለዚሁ ስራቸው የሚያግዛቸውን የመስክ ጉብኝት አድርገዋል። ከትናንት በስቲያ በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት የዝኆኖቹን መኖሪያ ጎብኝተዋል። ከአቶ ኃይለማርያም ጋር በጉብኝቱ የተሳተፉት የቀድሞው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አለማየሁ አሰፋ የፕሮጀክቱ የሥራ ኃላፊ መኾናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፖርክ የገብኝቱን ዓላማ አሰመልክቶ በጉብኝቱ ወቅት በተደረገው ገለጻ መሰረት በክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የተቋቋመና በሳቸው የቦርድ ሰብሳቢነት እንዲሁም በባለቤታቸው ክብርት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ሀላፊነት የሚመራው ግብረ ሰናይ ድርጅት በእናቶችና ህጻናት ጤና እንዲሁም በተፈጥሮ ሀብትና ብሄራዊ ፓርኮች ጥበቃና ልማት ዙሪያ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ለማከናወን በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ በሆነው የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክና አካባቢው ቅድመ ምልከታ ለማካሄድ ሲሆን ይሄንኑ ዓይነት የመስክ ጉብኝት በዛሬው ዕለትም በማዜ ብሔራዊ ፓርክ አድርገዋል።

 

የአቶ ኃይለማርያምና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በእነዚህ እና በሌሎች የሚካተቱ ብሔራዊ ፓርኮች በዋናነት በፓርኩ ልማትና በፓርኩ አጎራባች አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ኑሮ ለማሻሻል እንደሚሰራ የድሬ ቲዩብ መረጃ ሰጪዎች ገልፀዋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top