Connect with us

አትሌት አባዲ ሃዲስ አረፈ

አትሌት አባዲ ሃዲስ አረፈ
Photo: Facebook

ስፖርት

አትሌት አባዲ ሃዲስ አረፈ

በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮችን ማለትም በኦሎምፒክና፣ በዓለም ሻምፒዮና ሀገሩን በመወከል የሚታወቀው የ22 ዓመት ወጣት አትሌት የሆነው አባዲ ሀዲስ በህመም ምክንያት በመቀሌ ሃይደር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 26/2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና መላ ሠራተኞች የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን በመግለጽ ለአትሌቱ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት ተመኝተዋል፡፡

አትሌት አባዲ ሃዲስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ጥር 27 ቀን 1990 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን የአትሌቲክሰ ህይወቱን በእንዳመሆኒ የአትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ጣቢያ የጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በማይጨው አትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መደበኛ ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ ትራንስ ኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ክለብ በመቀላቀል ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በውጤታማነት ክለቡን፣ ክልሉንና ሃገሩ ሲያስጠራ የነበረ ሲሆን ካስመዘጋባቸው ድሎችም ውስጥ፡-

በኦሎምፒክ ጨዋታዎች

• በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2016 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በ10000ሜትር በ27፡36.34 በሆነ ሰዓት 15ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡

ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና

• በዶካ ኳታር በተካሄደው የ2019 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ5000ሜትር ተሳትፏል

• በለንደን በተካሄደው የ2017 የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ26፡59.19 በሆነ ሰዓት 7ኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡

በዓለም አገር አቋራጭ

• በኡጋንዳ ካምላ በ2017 በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአዋቂ ወንዶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በ28፡43 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሃስ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች

• በሞሮኮ ራባት በ2019 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ10000 ሜትር በ28፡27.38 7ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን

በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና

• በ2016 በተካሄደ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በ10000ሜትር በ28፡43.2 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀበት ከተወዳደረባችው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአትሌት አባዲ ሀዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በነገው እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክሰ ፌዴሬሽንና የክለቡ አመራሮችና ሌሎች ኃላፊዎች በተገኙበት በትውልድ ስፍራው ይከናወናል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top