Connect with us

በሶስት ቀናት ብቻ ለሞጣ ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ

በሶስት ቀናት ብቻ ለሞጣ ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

በሶስት ቀናት ብቻ ለሞጣ ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ

ለሞጣ ተጎጂ ሙስሊሞች ድጋፍ እስካሁን በካሽ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ ቃል መገባቱ ተሰማ። ድጋፉ በአይነት የተሰጡ ድጋፎችን ሳይጨምር በአጠቃላይ ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ለመስብሰብ መቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገልፀዋል።

በቂ ዝግጅት ባልተደረገበትና ሰፊ ጊዜ ተስጥቶት ባልተሰራበት ተጨባጭ እንዲሁም የህዝብ ናቸው ተብለው የሚታሰቡት የመንግስት የሚዲያ ተቋማት ተገቢውን ሽፋን ሳይሰጡት ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት በሶስት ቀን ውስጥ ይሄን ያህል ከፍተኛ ግምት ያለው ገንዘብ መሰብሰበ መቻሉን ሳያደንቁና ሳያመሰግኑ ማለፍ እንደማይቻል ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በሶሻል ሚድያ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

“በተለይ ደግሞ ጠንካራ የአሰራር መዋቅር ሳይኖር በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ መቶ ብር እና ሁለት መቶ ብር ተለቅሞ በአግባቡ ወደ ተከፈተው አካውንት እንዲገባ በማድረግ የዚህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ማስመዝገብ መቻሉን እያየን በህዝቡ ተሳትፎ አለመደመም አይቻልም፡፡

የኑሮ ውድነት የህዝባችን ራስ ምታት በሆነበትና የንግዱ እንቅስቃሴ በተቀዛቀዘበት ወቅት በዚህ መልኩ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውም ሌላኛው አኩሪ ገጽታ ነው፡፡

ህዝባችን ለዚህ አኩሪ ተሳትፎውና ዘመን ተሻጋሪ ተግባሩ የላቀ ምስጋና ብቻ ሳይሆን የላቀ ክብርም ይገባዋል” ሲሉ ኡስታዝ አህመዲን ፅፈዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top