Connect with us

በኮምፒውተር ሥርዓት የዘር ማጥፋት እና በስብእና ላይ የሚፈፀሙን ወንጀሎች እስከ ሰባት ዓመት ሊያስቀጡ ነው

በኮምፒውተር ሥርዓት የዘር ማጥፋት እና በስብእና ላይ የሚፈፀሙን ወንጀሎች እስከ ሰባት ዓመት ሊያስቀጡ ነው
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በኮምፒውተር ሥርዓት የዘር ማጥፋት እና በስብእና ላይ የሚፈፀሙን ወንጀሎች እስከ ሰባት ዓመት ሊያስቀጡ ነው

የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ የዘር ማጥፋት እና በስብእና ላይ የሚፈፀሙን ወንጀሎች ማነሳሳት እስከሳባት ዓመት የሚደርስ ቅጣትን ጣለ፡፡

ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው ማንኛውም ሰው የዘር ማጥፋትን በአንድ ዘር፣ ብሄር፣ ዜጋ ወይም ሃይማኖት ላይ በ ፅሁፍ፣ ቪድዮ፣ ድምፅ፣ ምስል ወይም በማንኛውም አይነት መንገድ በ ኮምፒዩተር ስርአት ያነሳሳ፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ላይ በ ፅሁፍ፣ ቪድዮ፣ ድምፅ፣ ምስል ወይም በማንኛውም አይነት መንገድ በ ኮምፒዩተር ስርአት ያነሳሳ፣ጦርነትን በ ፅሁፍ፣ ቪድዮ፣ድምፅ፣ምስል ወይም በማንኛውም አይነት መንገድ በ ኮምፒዩተር ስርአት ያነሳሳ ከ ሶስት አመት እስከ ሰባት አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡

በኢትዮጵያ የሕግና የፍትህ ጉዳይ አማካሪ ምክር ቤት የሚዲያ ጥናት ቡድን የመረጃ ነፃነትና የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላትና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ሰሞኑን ምክክር አካሂዷል፡፡

በሕዝብ ደህንነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በተመለከተም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀፅ 257 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ሰው ሆነ ብሎ በህብረተሰቡ መካከል አመጽ፣ ሁከት ወይም ግጭት እንዲፈጠር የሚያነሳሳ ጽሁፍ፣ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ድምጽ ወይም ማንኛውንም ሌላ ምስል በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ያሰራጨ እንደሆነ ከሦስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል ይላል፡፡

የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅ አዋጅ የ ሐሰተኛ ወሬዎችን በኮምፒውተር ሥርዓት ማሰራጨት እስከ ሶስት ዓመት እስራት ያስቀጣል፡፡

“ማንኛውም ሰው ሆነ ብሎ ወይም በ ከፍተኛ ቸልተኝነት በ ህዝብ ላይ ድንጋጤን አለመረጋጋትን ወይም አመፅን ሊያስከትል የሚችል ሃሰተኛ መረጃዎችን በ ኮምፒዩተር ስርአት በፅሁፍ፣ ቪድዮ፣ድምፅ፣ ወይም በምስል ወይም በማንኛውም አይነት መንገድ ያሰራጨ ከ ሦስት አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከ ብር 50 ሺ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል”

ረቀቅ አዋጁ በተጨማሪም የጥላቻ ንግግሮችን ማነሳሳት ስለመከልከሉ በሚል “ማንኛውም ሰው በ አንድ ዜጋ፣ ብሄር፣ዘር፣ሃይማኖት፣ፆታ፣ አካል ጉዳተኝነት እና በተመሳሳይ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የጥላቻ ንግግርን በ ፅሁፍ፣ ቪድዮ፣ድምፅ፣ምስል ወይም በማንኛውም አይነት መንገድ በ ኮምፒዩተር ስርአት ያነሳሳ ከ ሦስት አመት ባልበለጠ ቀላል እስራት ወይም ከ ብር 50 ሺ ባልበለጠ የገንዘብ ቅጣት እንደሚቀጣ ደንግጓል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top