Connect with us

ንጉሱ ጥላሁንም “ከታገቱበት” ይፈቱ…!?

ንጉሱ ጥላሁንም "ከታገቱበት" ይፈቱ...!?
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ንጉሱ ጥላሁንም “ከታገቱበት” ይፈቱ…!?

ንጉሱ ጥላሁንም “ከታገቱበት” ይፈቱ…!? | (ታምሩ ገዳ)

ከአንድ ወር በፊት ወለጋ፣ደምቢ ዶሌ ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው እጣፈንታቸው ዛሬ ድረስ በውሉ ያልታወቀው የደምቢ ዶሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ ከወላጆቻቸው እና ከቤተሰቤቻቸው አልፎ መላው ኢትዮጵያኖችን እያነጋገረ ይገኛል።

ሀኔታውን እጅግ ያወሳሰበው እና የብዙዎች ስሜትን በእጅጉ የጎዳው ደግሞ የወጣት ተማሪዎቹ መታገት በተስማ ማግስት ወደ ሚዲያዎች ብቅ ብለው” ሀያ አንዱ ተማሪዎች ተለቀዋል፣የተቀሩትን ለማስለቀቅ በሽማግሌዎች አማካኝነት በድርድር ላይ ነን”ያሉት የጠ/ሚ/ሩ የሴክሬት ሹም የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጉዳይ ነው።

የአጋቾቹ ማንነት እና አላማን ሳይገልጹ አስራ ሶስት ሴቶች እና ስምንት ወንድ ተማሪዎች ከአጋቾቻቸው መለቀቃቸውን ብቻ ያበሰሩት አቶ ንጉሱ ይህንን ቃላቸውን ለተማሪዎቹ ወላጆች እና ለህዝቡ ይፋ ካደረጉ ወደ ሁለት ስምንት ሊቆጠር ቢጠጋም ተለቀቁ ስለ ተባሉት ሆነ በአጋቾች እጅ ይገኛሉ ስላሉዋቸው ስድስቱ ተማሪዎች ወቅታዊ ሁኔታ እንዲገልጹ ከተለያዩ የአገር ውስጥ እና አለማቀፍ ተደራሽነት ካላቸው ሚዲያዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎች ቢደረ ግላቸውም እነዚያ ደንቢ ዶሎ ላይ እንደዋዛ ደብዛቸው እንደጠፋው ልጆቻችን እና ወገኖቻችን የአቶ ንጉሱ ጥላሁንም ዱካቸው ከጠፋ ከአንድ ሳምንት በላይ ተቆጥሯል።

በለውጡ ዋዜማ ሆነ ማግስት የተለያዩ መረጃዎችን በድምጽ ይሁን በአካል ለመገናኛ ብዙሃናት በማድረስ እና በሚዲያ ወዳጅነታቸው የሚታወቁት የቀድሞው የአዴፓ ቃል አቀባይ ፣የወቅቱ የጠ/ሚ/ሩ የፕሬስ ሴክሬያት ሐላፊው አቶ ንጉሱ በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተከታዮቻቸው ሰሞነኛ መጥፋት፣ወደ ሚዲያዎች ቀርበው እንቅጩን ለመናገር ድፍረት እና ሞራሉን ማጣታቸው ብዙዎችን” አቶ ንጉሱ አረጉ?፣ ሰረጉ?፣እርሳቸውም ከታገቱ በአስቸኳይ ይፈቱልን “ለሚሉ ጥያቄዎች እና ጥርጣሬዎች ዳርጓቸዋል።

በአገራችን ባህል እና እምነት እንኳን ከአብራክ የወጣ ልጅ ታፍኖ ነበር መባሉ ቀርቶ ፣ ያሳደጉት ከብት እንኳን ለአፍታ ሲጠፋ ባለቤት ይሸበራል፣ በሀሳቡ እና በእግሩም ብዙ ቦታን ይረግጣል።ሰሞኑን ደንቢዶሎ ላይ ታፍነው ደብዛቸው የጠፋው ተማሪዎች ቤተሰቦችም ስሜታቸው ከዚህ ውጪ አይሆንም።

መንግስት የዜጎቹን ደህንነት በቅድሚያ ማስጠበቅ ግዴታው እንደመሆኑ ሁሉ ተገቢውን መረጃም ለህዝቡ በተለይ ደግሞ ለተጎጂ ቤተሰቦች በተለየ ፍጥነት እና እንክብካቢ የማድረስ ህገመንግስታዊ እና ሞራላዊ ግዴታ አለበት።በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፈጣን መረጃዎችን በትዊተር፣በፌስ ቡክ ገጹ የሚያደርሰን የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደርም ቢሆን ለእውቀት ገበያ ወጥተው ደብዛቸው በጠፋው ልጆቻቸው ጉዳይ እንባቸው እና ስጋታቸው ዛሬ ድረስ ያልተቋረጠው፣ ምን ይመጣልን ይሆን ብለው እንቅልፍ በፊታቸው ዘወር ያላለው ለእነዚያ ምስኪን ወላጆች እና ቤተሰቦች ማስፈራራሪያ እና አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል ተግሳጽ ሳይሆን ትክክለኛውን እና ወቅታዊ መረጃን ሊነግራቸው እና ሊያካፍላቸው የግድ ይላል።

ከወላጅ ያፈነገጠ መረጃን በቢሮ ውስጥ ሸሽጎ መቀመጥ ትርፉ በመንግስት ላይ ጥላቻ እና ጥርጣሬን ከመጨመር ውጪ ለማንም የፓለቲከኛ ጎራ አይጠቅምም የሚሉ ወገኖች በርካታዎች ናቸው ። የቃላት ሽንገላ እና ክሸናን ብቻ ሳይሆን እውነቱን ተናግሮ ከመሸመት የማደር ባህልን ከመንግስት እና ከፓለቲከኞቻችን ይጠበቃል ።አቶ ንጉሱ ጥላሁንም ቢሆኑ የዝምታ ድባባቸውን ፈትተው ደምቢዶሎ ላይ ደብዛቸው ስለጠፋው ልጆች ወቅታዊ ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ያቀብሏቸው።እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ከዚህ የበለጠ አገራዊ ፣ ህዝባዊ እና ወገናዊ ጉዳይ የቱ ጋር ነው ያለው? የተማሪዎች እና የወላጆች ስጋትም ደምቢ ዶሎ ላይ ይብቃ ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top