Connect with us

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም በህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎችን ተመልክቷል።

አቶ አበበ ጎዴቦ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት፥ የሽብር ድርጊት በሰው ህይወት፣ አካል እና ስነ ልቦና እንዲሁም ንብረትና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ከመጡ የስራ ሃላፊዎች፣ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የፍትህ አካላት፣ ከህዝብ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዝርዝር ውይይት ማድረጉንም አንስተዋል።

በዚህም ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን እና ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መገኘታቸውን አውስተዋል።

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተስተዋለ ያለውን ችግር ለማስወገድ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ረቂቅ አዋጁ ቢጸድቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አብራርተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም የቀረበውን ሪፖርት በተመለከተ መስተካከል ይገባቸዋል ያሏቸውን ሃሳቦች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።(ምንጭ፡-ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top