Connect with us

የነገሥታቱን ሕይወት በነገሥታቱ ግቢ፤ ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳለች

የነገሥታቱን ሕይወት በነገሥታቱ ግቢ፤ ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳለች

ባህልና ታሪክ

የነገሥታቱን ሕይወት በነገሥታቱ ግቢ፤ ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳለች

የነገሥታቱን ሕይወት በነገሥታቱ ግቢ፤ ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳለች

ጅማ፣ መቐለ፣ ሀረር ዝግጁ ናችሁ? ይላል ቱሪዝም ኢትዮጵያ
**
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጎንደር የዘንድሮን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በጎንደር አብያተ መንግስታት ግብረ ህንጻ ያሰናዳችውን ሕይወት በአብያተ መንግስታት ዝግጅት ማስገምገሟን ተከትሎ ቀጣዮቹ መዳረሻዎች ጅማ መቐለና ሀረር ናቸው ሲል የቱሪዝም ኢትዮጵያን አዲስ የጎብኚ ማቆያ ዘዴ እንዲህ ተርኮታል፡፡ l ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዮብ

ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳለች፡፡ ከተማዋ የጥምቀት ድባብ ናኝቶባታል፡፡ ሆታዋን ሰማይዋ ናፍቆታል፡፡ ዝማሬዋን ለማየት ጎዳናዎቿ ጓጉተዋል፡፡ ጥምቀት ጥር አስር ተጀምሮ የቃና ዘገሊላ ዕለት የሚጠናቀቅ መሆኑና በጥምቀቱ ድባብ ሙሉ ጥርን የውጪ ጎብኚ ይዞ አለማክረሙ ድክመታችን ነበር፡፡ ይሄንን ለመቅረፍ የጎንደሩ ባህል ማዕከላ መላ ዘይዷል፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ደግሞ አጋር ነው፡፡

ነገሥታቱ ግቢ በጠዋት ደረስን፤ ከወትሮው ይለያል፡፡ ደጃፉ ሞገስ ባላቸው ጃኖ ለባሽ ዘቦች ተቀጥሯል፡፡ ወደ አልኖርኩበት ዘመን መለሰኝ፡፡ ዓላማው የነገሥታቱን ግቢ የዚያን ዘመን ሕይወት ዛሬ ማሳየት ነው፡፡ ይሄንን የሚመለከት ተጣድፎ አይወጣም፡፡ ፋሲል ግንብ ሕይወት አለው፡፡ ፈረሰኞቹ የፈረስ ማቆሚያው ላይ ናቸው፡፡ ቅጥሩ ሰውን ወደ ኋላ ይመልሳል፡፡ ብዙ ወጣቶች አዲሱን የጎብኚ ማቆያ ስልት ለመከወን ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡

 

ዓላማው ጎብኚ በምድረ ቀደምቷ ሀገር ረዘም ያለ ቀናት እንዲያሳልፍ ማድረግ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ኩነት የሙከራ ዝግጅቱ በጎንደር ተጀምሮ ወደሌሎችም ይቀጥላል፡፡ የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች እንደ ጎንደር ቤተ መንግስት ሁሉ ጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት እንዲሁ ሕይወት ይዘራበታል፡፡

መቐሌና ሀረርም እንዲህ ያለው እንግዳ የማቆያ ጥበብ የሚተገበርባቸው ይሆናል፡፡
የጎንደር ባህል ማዕከል ለወራት ሽር ጉድ ብሏል፡፡ የተለያዩ ቡድኖች በተለያዩ ዝግጅቶች ተዋቅረዋል፡፡ የትዕይንቱ ማብሰሪያ ታህሳስ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ሆኗል፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከነባለቤታቸው በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት ፕሮጀክት ሆነ፡፡

ለጥምቀት ያልሆነ በምትለው መዲና ይህ ሌላ ተጨማሪ እሴት ነው፡፡ አፍ የሚያስከፍት ትዕይንት ይሆን ዘንድ ሀገር እንዲህ ካለው መላ ጎን መቆም ይኖርበታል፡፡ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top