Connect with us

የኤክሳይዝ ታክሱ ረቂቅ አዋጅ በትምባሆ ላይ የጣለው 30 በመቶ ታክስ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል ተጠየቀ

የኤክሳይዝ ታክሱ ረቂቅ አዋጅ በትምባሆ ላይ የጣለው 30 በመቶ ታክስ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል ተጠየቀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኤክሳይዝ ታክሱ ረቂቅ አዋጅ በትምባሆ ላይ የጣለው 30 በመቶ ታክስ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለሥልጣን ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የደረሰው የኤክሳይዝ ታክስ ላይ ትምባሆን በተመለከተ የተጣለው ታክስ ትምባሆ እያደረሰ ያለው ዘርፈ ብዙ ጉዳት እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ሲል ነቀፈ፡፡

ባለሥልጣኑ በትላንትናው ዕለት ከተለያዩ ሚዲያዎች ከተውጣጡ ጋዜጠኞች ጋር በአዳማ ከተማ ባደረገው ምክክር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ከይረዲን ረዲ የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር የዓለም የጤና ድርጅት የትምባሆ ኮንቬንሽን ማዕቀፍን ዓላማ ለማሳካት ያስችል ዘንድ 70 በመቶ የሚጠጋው የትምባሆ ችርቻሮ ዋጋ ታክስ እንዲሆን እንደሚመክር አስታውሰዋል፡፡ ሆኖም በኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ የተቀመጠው የታክስ መጠን 30 በመቶ እና በፓኮ 5 ብር ብቻ መሆኑ እጅግ ዝቅተኛና ትምባሆ እያደረሰ ያለው ጉዳት እንዲቀጥልና እንዲስፋፋ ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ከይረዲን አያይዘውም በትምባሆ ላይ ሊጣል የሚገባው የኤክሳዝ ታክስ መጠን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአዋጅ ቁጥር 822/2006 ዓ.ም ያጸደቀውን የትምባሆ ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽንና የአዋጅ ቁጥር 1112/2011 ሊያሳካ በሚችል መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከትምባሆ ጋር በተያያዘ 17 ሺ ሕዝብ እንደሚሞት በመድረኩ ላይ የቀረቡ ጥናቶች የጠቆሙ ሲሆን የኤክሳይዝ ታክስ ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች እስከ 500 ፐርሰንት ጠንካራ ታክስ መጣል መቻሉም በአድናቆት የምናየው ቢሆንም በሌላ በኩል ትውልድ እያጠፋ ያለውን ትምባሆ በ30 በመቶ ዝቅተኛ ታክስ ማለፉ ኢ ፍትሐዊ ስለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ባለሥልጣኑ የኤክሳይዝ ታከስ መጠኑ ከ30 ወደ 50 በመቶ እንዲሆን እና በፓኮ ከ5 ብር ወደ 8 ብር እንዲያድግ ፍላጎት እንዳለው የጠቆመ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊ ጋዜጠኞች መካከል አንዳንዶቹ የኤክሳይዝ ታክስ የዓለም የጤና ድርጅት በሚደግፈው እስከ 70 በመቶ የማያድግበት ምክንያት ምንድነው፣ ማንንስ ለመጥቀም ነው ሲሉ ጠይቀዋል

በየካቲት ወር 2011 ዓ.ም የሕዝብን ተወካዮች ም/ቤት በአፍሪካ ጠንካራ ከሚባሉ የትምባሆ ሕጎች መካከል አንዱ የሆነውን የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎችን የያዘውን የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡ በአዋጁ የተካተተው ሕግ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ካሉት ጠንካራ ሕጎች መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሆኖ በመገኘቱ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከዓለም የጤና ድርጅት የዕውቅና ሰርተፊኬት ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top