Connect with us

በሐይማኖት መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ልንጠየፈው የሚገባ የጽንፈኞች አካሄድ እንደሆነ ተገለፀ

በሐይማኖት ተቋማትና በተከታዮቻቸው መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ልንጠየፈው የሚገባ የጽንፈኞች አካሄድ እንደሆነ ተገለፀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በሐይማኖት መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ልንጠየፈው የሚገባ የጽንፈኞች አካሄድ እንደሆነ ተገለፀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአማራ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር በሃይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው በሐይማኖት ተቋማትና በተከታዮቻቸው መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ልንጠየፈው የሚገባ የጽንፈኞች አካሄድ ነው ብለውታል።

ሰሞኑን እየተስተዋላ ያለውን በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት በተመለከተ ጠቅላይ ሚስትር ዶክተር አብይ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በብልጽግና ጎዳና ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሀገራችንን የቆየ የሃይማኖቶች የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶች ከእንግዲህ ቦታ የላቸውም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም እንዲህ ያሉ የፈሪ አካሄዶችን አጥብቄ አወግዛለሁ፤ ከፋፋይ አጀንዳዎችን መረዳትና መጠየፍ የጋራ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ ያስችላል፤ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንም የመከባበርና አብሮ የመኖር ጥልቅ ዕውቀታችሁን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል::

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ ላይ በየትኛውም የሃይማኖት ተቋማትና ሃይማኖተኞች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚደረግ ተግባር ከህዝባችን አብሮነት ጋር የሚጋጭ እኩይ ተግባር በመሆኑ ህዝባችን በጋራ ሊያወግዘው ይገባል፤ ህብረተሰቡም በእንዲህ ያለው የማይገባ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ አካላትን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ሽመልስ አክለውም መንግስትም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በእንዲህ ያለው እኩይ ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ጽንፈኛ አካላት ላይ ተገቢወን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በመግለጫቸው ላይ አስምረው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሰው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ላይ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት በተመለከተ እንዳሉት ድርጊቱ በፍቅርና በአንድነት አብረው የኖሩትን የሁለቱን ሃይማኖት ተከታዮች ለማጋጨት የተደረገ ሴራ ነው።

ኢትዮጵያ አንደነቷን የጠነከረ ታላቅ ሀገር እንዳትሆን የሚጥሩ ጠላቶቿ ሁሉ ቀዳሚ ዒላማቸው የሃይማኖት ተቋማትና ተከታዮቻቸው ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በእንደዚህ ያለው ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ማንኛውንም አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብ የጸጥታ ሃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ :- ኢፕድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top