Connect with us

“ያሳዝናል!” -በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

"ያሳዝናል!" -በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“ያሳዝናል!” -በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

“ያሳዝናል!”
(በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

ሞጣ ላይ የተፈጸመዉ ነገር አሳዛኝም፤ አሳፋሪም ነው። የሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቃጠሎ አደጋ ገጥሞት በምእመናን ርብርብ ቶሎ ሊጠፋ ችሏል። ነገሩን ከሞጣ ሙስሊሞች ጋር የሚያገናኘው ነገር አልነበረም። የሞጣ ሙስሊሞችኮ በአካባቢው ሁለቱን እምነቶች ሊያጣሉ የሚያስቡ አካላት መኖራቸውን ቀድመው ለክርስቲያኖችና ለመንግሥት ያሳሰቡ ናቸው። የጻፉት ደብዳቤ ምስክር ነው።

የአካባቢው መስተዳድር የሞጣን ሙስሊሞች ጥቆማ በቸልታ ተመለከተው። በዚህ መሐል ሞጣ ጊዮርጊስ ባልታወቀ ምክንያት የመቃጠል አደጋ ገጠመው። ጢሱን በጉልላቱ ላይ ያዩት ሰዎች አስቸኳይ ጥሪ በማቅረባቸው ቶሎ ርምጃ ሊወሰድ ቻለ።

ከዚያ በኋላ መስጊዶችን ማቃጠልና የሙስሊም የንግድ ተቋማትን ማቃጠል ተጀመረ። በሌላ አካባቢ የተቃወምነው ነገር ተገልብጦ ተፈጸመ። አሳፋሪ፣ አሳዛኝ። ”ችግር እንዳይከሠት ንቁ፤ አንዳንድ ነገሮች እያየን ነው” ብለው ሲያስጠነቅቁ የነበሩ ሙስሊም ወገኖችን ባጎረስኩ ተነከስኩ ዓይነት የሞኝ ብሂል መጉዳት በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል።

አሁን፦
1.እንረጋጋ
2.የአካባቢው መስተዳድር የሞጣ ሙስሊም ወገኖቻችን የሰጡትን ጥቆማ ለምን ቸል እንዳለው ክልሉ አጣርቶ ርምጃ ይውሰድ
3. አጥፊዎቹን በጋራ አጋልጠን እንስጥ
4. የጠፋውን በጋራ እንመልስ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top