Connect with us

የፖሊስ አባሉ ሰው በመግደል ወንጀል ተቀጣ

የፖሊስ አባሉ ሰው በመግደል ወንጀል ተቀጣ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የፖሊስ አባሉ ሰው በመግደል ወንጀል ተቀጣ

የትራፊክ አባሎች ቁም ሲሉት እንቢ ብሏል በሚል ምክንያት በቦሌ ክፍል ከተማ ወረዳ 07 አካባቢ የሰው መግደል ወንጀል የፈጸመው የፖሊስ አባል ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡

ተከሳሽ ም/ሳጅን ታዘባቸው ንጋቱ የፖሊስ አባልነት መተዳደሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 268/2005 አንቀጽ 3/2፣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ ስራ ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ በሌላ የክስ ጉዳያቸው በመታየት ላይ ካሉት ሶስት ተከሳሾች ጋር በመሆን ተከሳሽ የፖሊስ ሰራዊት እንደመሆኑ የሌላውን ሰው ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እያለበት ስራውንም በማስተዋል፣ በትህትና እና በታጋሽነት ማከናወን እንዲሁም ከሀይል አጠቃቀም እንጻር የተለየ እንቢተኝነት ያላሳየውን ሟች ከሕግ ተገዢ እናደርጋለን በሚል ሰውን ለመጉዳት ፍፁም ፈቃደኛ በመሆን ጨካኝነቱን፣ ነውረኝነቱን እና አደገኛነቱን በሚያሳይ ሁኔታ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል፡፡

ተከሳሽ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው አለማየሁ ህንጻ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሟች ወጣት ሮቤልን ጃክሮስ አደባባይ ለመንገድ ስራ ተዘግቶ የነበረን መንገድ ሟች በሚያሽከረክረው መኪና ጥሶ አልፏል፣ የትራፊክ አባሎች ቁም ሲሉት እንቢ ብሎ አምልጧል በሚል ምክንያት ኮ/ብል ከፍያለው ደምሴ እና ኮ/ብል አብረሀም በቀለ የተባሉት በያዙት የጦር መሳሪያ ጀርባውን ደጋግመው ሲመቱት ኮ/ብል ላቃቸው ባምላክ የተባለውን በዱላ እና በጫማ በመረጋገጥ በጭቅላቱ ላይ ባደረሰበት ጉዳት ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽ በወንጀል ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸመው ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅርቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ በፈፀመዉ ወንጀል ተጠያቂ መሆን የሚችልበትን በፖሊስ የምርምራ መዝገብ መሰረት የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎችን በመያዝ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል::ተከሳሽ በሌለበት ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል::

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በማቅለያ በመቀበል በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል::

(ምንጭ:-ፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top