Connect with us

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ

ለሰራተኞች በሚከፈል ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ፡፡

ታህሳስ 8 ፣ 2012 ዓ.ም. ፤ ለሰራተኞች በሚከፈል ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ሰይድ ገልጸዋል ፡፡

ፓርኩ 2147 ሰራተኞችን ያቀፈ ሲሆን ፣ በአንደኛው ሩብ አመት 628 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ 579 የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በደመወዝ ማነስና ተያያዥ ምክንያቶች በሩብ አመቱ 526 ቱ ፓርኩን ለቀው እንደወጡ ኃላፊው አክለዋል ፡፡
የችግሩ አሳሳቢነት ፓርኩን ሊያዘጋው እንደሚችልና በፍጥነት የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ይደረግ ብለን ለሚመለከተው አካል ብናሳዉቅም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል አቶ አህመድ ፡፡

ፓርኩ በአንድ አመት ከአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ሰባት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት የተለያዩ ምርቶችን ወደ ዉጭ ኤክስፖርት ማድረግ እንደቻለ አቶ አሕመድ ገልጸዋል ፡፡

አንድ የአለቀለት ሙሉ ሱፍ ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ሲወጣ ከ 5 እስከ 8 የአሜሪካን ዶላር እንደሆነ የገለጹት አቶ አህመድ ፣ በአለም ገበያ ግን ከ 300 እስከ 1700 የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ጠቅሰዋል፡፡

እንዲህ አይነት አሰራሮችን ፓርኩን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጉት ስለሚገኙ እንዲቆሙ የሚመለከተው አካል ሊሰራበት ይገባል ብለዋል አቶ አህመድ ፡፡

ይህ የተገለጸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከትና ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የገቡ አምራች ኩባንያዎች አፈጻጸማቸውን ከማሳደግ አኳያ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው ፡፡

የኤክስፖርት አፈጻጸሙ የተሻለ መሆኑ ፣ ኤክፖርት ተኮር ምርቶች መመረታቸው ፣ የፓርኩን ደህንነት ለመጠበቅ ጥብቅ ክትትል መደረጉ ፣ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋራ ስራዎች በጋራ እየተሰሩ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ ከገለጻቸው መካከል ተጠቃሾች ናቸው ፡፡

ቋሚ ኮሚቴ የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር ፣ የስራ እድል ፈጠራ አነስተኛ መሆኑ ፣ የሰራተኞች የቤት ግንባታ መጓተትን በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ጠቁሟል ፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተገለጹላቸውን አስተያየቶች ተቀብለው በትኩረት እንደሚሰሩባቸው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:-  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top