Connect with us

እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የተጠረጠሩበት የወንጀል መዝገብ ተዘግቶ በነፃ ተሰናበቱ

እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በነፃ ተሰናበቱ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የተጠረጠሩበት የወንጀል መዝገብ ተዘግቶ በነፃ ተሰናበቱ

እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የተጠረጠሩበት የወንጀል መዝገብ ተዘግቶ በነፃ ተሰናበቱ

ከሰኔ 15/2011ዓ.ም ከከፍተኛ መሪዎች ግድያ ጋር በተያያዘ ዋናውን ጉዳይ በማቀነባበርና በመምራት ተጠርጥረው በእስር የቆዩት እነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል በአምላክ ተስፋ እና ኮማንደር ጌትነት ሽፈራው በተጠረጠሩበት ወንጀል በምርመራ መዝገቡ ላይ ዐቃቤ ሕግ የአያስከስስም ውሳኔ ሰጠ፡፡

ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት ወንጀል በጊዜ ቀጠሮ ምርመራው ሲካሄድ ቆይቶ የተጠረጠሩበት የምርመራ ውጤት ዋስትና የማይከለክል በመሆኑ ከጥቅምት 12/2012 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ተለቅቀው ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ በተጠርጣሪዎች ላይ የተደረገው ምርመራ ዐቃቤ ሕግ ተጠቃሎ ደርሶት የምርመራ መዝገቡ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ለመመሥረት የሚያስችል የወንጀል ድርጊቱን የማቀነባበር፣ የመምራት እና ኃላፊነታቸው ስላለመወጣታቸው የሚያረጋግጥ የሰውና የቴክኒክ ማስረጃ ባለመገኘቱ በአንፃሩ ወንጀሉ ከተፈፀመ በኋላ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት በማስረጃ በመረጋገጡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ዐቃቤ ሕግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/ መሠረት የክስ አይቀርብም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንዲመለስላቸውም ወስኗል፡፡

(ምንጭ፡- የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሀን ድርጅት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top