Connect with us

አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሠራተኛ በእሥራት ተቀጣች

አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሠራተኛ በእሥራት ተቀጣች
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሠራተኛ በእሥራት ተቀጣች

በአዲስአበባ ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ሁለት ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡

በ1ኛ ክስ ተከሳሽ መሰረት ነገሰ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው ሉዋም ሱቅ ውስጥ ሟች እርግብ ገ/ክርስቶስ ቤት ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ እየሰራች በነበረችበት ወቅት ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሯ በተደጋጋሚ ጊዜ ስልክ በመደወል ሟችን በተኛችበት ግደያት በማለት ሲነግራት እሷም በእለቱ ሟች ወደ ተኛችበት ክፍል በመሄድ በብርድ ልብስ አፍና የጉሮሮዋ ቧንቧ እንዲደፈን በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ በፈጸመችው የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳለች፡፡

በ2ኛ ክስ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ለ) እና 669 (2) (መ) በመተላለፍ ተከሳሽ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ሟችን ከገደለቻት በኋላ ያልተያዘውን ግብረአበሯ ስልክ በመደወል ጠርታ ወደ ሟች ሱቅ በመግባት 6000 ብር እና ግምቱ ያልታወቀ ገንዘብ እንዲሁም የዋጋ ግምቱ ብር 1650 ብር የሆነ ስልክ ከወሰዱ በኋላ ግብረ አበሯ ለተከሳሽ 2000 እና የሟችን የእጅ ስልክ የሰጣት የወሰደች በመሆኑ በፈጸመችው የግድያና ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሳለች፡፡

ተከሳሽ የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኃላ በሁለቱም ክስ ላይ የተጠቀሱትን ድርጊቶች አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች፡፡ዐቃቤ ሕግም እንደክሱ አቀራረብ የምስክሮች ቃል እንዲሳማ ለፍርድ ቤቱ ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ በቀረበባት ሁለት ክስ ጥፋተኛ ተባለች::

በመጨረሻም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን የዘወትር ፀባይ መልካም እንደነበር እና ቤተስብን የምትረዳ መሆኑን በማቅለያ በመያዝ በሁለቱ ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡(ምንጭ:-የፌ/ጠ/ዐ/ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top