Connect with us

ጠ/ሚ ዐብይ የወሰዱት የኖቤል ሽልማት ሜዳሊያ እና ዲፕሎማ በሙዚየም እንዲቀመጥ ወሰኑ

ጠ/ሚ ዐብይ የወሰዱት የኖቤል ሽልማት ሜዳሊያ እና ዲፕሎማ በሙዚየም እንዲቀመጥ ወሰኑ
Photo: Facebook

ዜና

ጠ/ሚ ዐብይ የወሰዱት የኖቤል ሽልማት ሜዳሊያ እና ዲፕሎማ በሙዚየም እንዲቀመጥ ወሰኑ

#ሰበር ዜና
ጠ/ሚ ዐብይ የወሰዱት የኖቤል ሽልማት ሜዳሊያ እና ዲፕሎማ በሙዚየም እንዲቀመጥ ወሰኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ 100ኛውን የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸንፈው ሰሞኑን ሜዳሊያውንና ዲፕሎማውን መቀበላቸው ይታወቃል፡፡ የዚህ ታሪካዊ የክብር ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ መወሰናቸው ተሰምቷል፡፡

ሜዳሊያውና ዲፕሎማው በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጠው የፊታችን እሁድ ታህሳስ 05 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት መሆኑንም የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በሽልማት መልክ ያገኙትን 30 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ምን ላይ እንደሚያውሉት እስካሁን በይፋ የገለጹት ነገር የለም፡፡

የዲፕሎማና የሜዳሊያ ሽልማቱ በሙዚየም መቀመጡ ወጣቱ ትውልድ መልካም አርአያነትን እንዲቀስም ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top