Connect with us

“አልቻልንም!” – የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝኩነት ኤጀንሲ

"አልቻልንም!" - የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝኩነት ኤጀንሲ
Photo: Facebook

ዜና

“አልቻልንም!” – የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝኩነት ኤጀንሲ

“አልቻልንም!”

አዲስ ፓስፖርቶች እየተሰጡ ቢሆንም የተገልጋዮችን ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በሩብ ዓመቱ ለአገልግሎት፣ ዲፕሎማቲክና መደበኛ ፓስፖርቶች 84 ሺህ አዲስ ፓስፖርቶች መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

የፓስፖርት እጥረቱ ዋነኛ ምክንያት የዶላር እጥረትና የአታሚ ድርጅቱ ችግር መሆኑን የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

በቂ ፓስፖርት ህትመት አለመከናወኑና የፓስፖርት እጥረት መኖሩ የተገልጋዩን ፍላጎት በሚያሟላና ብልሹ አሰራርን በሚቀንስ መልኩ አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም አሁን 1 ሚሊዮን ፓስፖርት እንዲታተም ታዟል፤ እየተጓጓዘም ይገኛል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

የፓስፖርት እጥረቱ ከተከሰተ በኋላ በ45 ቀን ሲሰጥ የነበረው መደበኛ ፓስፖርት ለ3 ወር ቀጠሮ በመስጠት እንዲስተናገድ እየተደረገ ነው ብሏል፡፡

የተወሰኑ ፓስፖርቶችንም ለህክምና፣ ለመንግስት ስራ የድጋፍ ደብዳቤ ለሚያቀርቡና ለከፍተኛ ግብር ከፋይ አስመጭና ላኪዎች ከአንድ ቀን እስከ አምስት ቀን በሆነ ጊዜ እየተስተናገደ ነው፡፡

ችግሩን በተወሰነ መልኩ ለመቀነስም ያለ ልደት ሰርተፍኬት በቀበሌ መታወቂያ ብቻ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት የልደት ሰርተፍኬትና መታወቂያ እንዲያመጡና በህገ ወጥ መልኩ መታወቂያ በማምጣት አገልግሎት ሲያገኙ የነበሩ አካላትን በመለየት ትክክለኛው ተገልጋይ ብቻ ፓስፖርት እንዲያገኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

ህብረተሰቡም በፓስፖርት አታሚ ድርጅት ምክንያት የፓስፖርት እጥረትና መዘግየት መፈጠሩን ተረድቶ ጊዜያዊ ችግሩ እስኪቀረፍ እንዲታገስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(ኢፕድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top