Connect with us

የሴት አካል ጉዳተኞች የሥራ ቅጥር ሁኔታ አካታች አይደለም ተባለ

የሴት አካል ጉዳተኞች የሥራ ቅጥር ሁኔታ አካታች አይደለም ተባለ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የሴት አካል ጉዳተኞች የሥራ ቅጥር ሁኔታ አካታች አይደለም ተባለ

የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በሁሉም ዘርፍ ተካታች ሆኖ መሰራት እንዳለበት በአዋጅ ቢቀመጥም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበራት ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሪት ዘነበች ጌታነህ እንደተናገሩት፤ ለአካል ጉዳተኞች በአዋጅ ሳይቀር ለተሰጣቸው መብት ትኩረት እየተሰጠው አይደለም። በተለይም ሴት አካል ጉዳተኞችን በሥራ ቅጥር ማሳተፍ ከልማት ግቦች አንዱ ተደርጎ ቢቀመጥም በአፈጻጸም ግን ሲተገበር አይታይም፡፡

ሴት የአካል ጉዳተኞች በብዙ ጫናዎች ውስጥ አልፈው ይመረቃሉ፡፡ ሙሉ እውቀት ኖሯቸውም ለአገራቸው ላበርክት ሲሉ የሚሰማቸው የለም፡፡ ይህ ደግሞ በተለይ የውሳኔ ሰጪው አካል ድክመት ነው ይላሉ ምክትል ፕሬዝዳንቷ፡፡

“ህግ ወጥቶ ተጠያቂነት ከሌለበት ማንም ሊተገብረው አይችልም፡፡ ስለሆነም የሴት አካል ጉዳተኞች በልማት ግብ ተካታችነታቸው የውሃ ሽታ ሆኗል” ሲሉም ነው ቅሬታቸውን የገለጹት።

ሴት የአካል ጉዳተኞችን ከህልማቸው ጋር የሚያገናኛቸውን አካል ይሻሉ ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቷ፤ ሥራቸው በአደባባይ ይታይ ዘንድ በተለይ ውሳኔ ሰጪ አካላት ከልማታዊ ግቦች አንጻር እያዩ የሚሳተፉበትን አማራጭ ሊያስተካክሉ እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቤ አቶ አለሙ ገብሬ በበኩላቸው፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ሴት የአከል ጉዳተኞች የተሰጣቸው የሥራ እድል እጅግ አናሳ ነው፡፡ በመሆኑም ለአገራቸው ማበርከት ያለባቸውን እንዳያደርጉ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

እንደ አቶ አለሙ ገለጻ፤ ፌዴሬሽኑ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የየድርሻውን መስራት አለበት፡፡ ከዚህ አኳያም ምክርቤቱ ከዚህ በኋላ ትርጉም ያለው ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ምንጭ:- ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top