Connect with us

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ኩራታችን፤ ስኬታቸው ደግሞ ስኬታችን ከሆነ …

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ኩራታችን፤ ስኬታቸው ደግሞ ስኬታችን ከሆነ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ኩራታችን፤ ስኬታቸው ደግሞ ስኬታችን ከሆነ …

“የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ኩራታችን፤ ስኬታቸው ደግሞ ስኬታችን ከሆነ፤ ድክመታቸው ድክመታችን መሆን ይኖርበታል፡፡” – ከሰለሞን ሃይሉ በድሬቲዩብ

የዶክተር አብይ የኖቤል ሽልማት ለደሃ ሀገር ትርጉሙ ብዙ ነው፡፡ በጦርነትና በርሃብ የዓለምን መገናኛ ብዙሃን ቀልብ የምትስበው ኢትዮጵያ በበጎ የምትነሳው ኦሎምፒክ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ለምርጫ መጭበርበር፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ለእርስ በእርስ ግጭት፣ ለብሔር ሽኩቻ ዜናዎች መግቢያ ነው፡፡

ኦስሎና ኢትዮጵያ እኩል ስማቸው የተነሳው በበጎ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ሲሆኑ ሥነ ስርዓቱ ደማቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ስሟ ከዳር ዳር እንዲነሳ በበጎ እንድትወሳ ታሪኳ እንዲፈተሽ እድል ፈጥሯል፡፡

እርግጥ ነው ምቀኝነታችን አሁን ዳግም ታይቷል፡፡ ለምሳሌ ዶክተር ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ጸሐፊነትን ሲወዳደሩ ተቃውሞ የተሰማው ከሀገር ልጅ ነበር፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኖቤል ዓይኑ የቀላ ምቀኛ ዳግም ስናይ ያው አንዱ ባህላችን ይሆን ያስብለናል፡፡

በሌላ በኩል ሚዲያውም ህዝቡም ኖቤሉ የኢትዮጵያ ነው እያለ ደጋግሞ ይሰብከናል፡፡ የምቀኛ አይናችንን አሽተን ከተመለከትነው እውነትም ኖቤሉ የኢትዮጵያ ነው፡፡ ወዲህ መሪዋ በሽልማት የሚያመጣው ብር ለሀገር ጠቃሚ ነው፡፡ ሽልማቱ እና ክብሩን ቢሆን ከመሪዋ እኩል ሀገር የምትጋራው መሆኑ ሽልማቱን የእኛ ያስብለዋል፡፡

ጥያቄው አንድ መሪ ሽልማት ሲያመጣና ሲሳካላት ሽልማቱ የሀገርና የህዝብ ነው ካልን፣ ሲያቅተው፣ ሲከብደው፣ ችግሩ መፍታት ጣር ሲሆንበትስ ያን ጉድለት ሀገርና ህዝብ የሚጋራው መቼ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስኬታማ ስራዎቻቸው የኢትዮጵያውያን ኩራት ናቸው ካልን አጎደሉት ያልናቸው፣ ቢሆን ብለን የምንመኘው፣ ሳይሟላ የቀረውንስ ለምን የሀገርና የህዝብ ጉድለት ነው ብለን ማየት አቃተን፤ ድላቸው ድላችን ከሆነ ሽንፈታቸው እንዴት የብቻቸው ሊሆን ይችላል?

ከዚህ ሽልማት መማር ያለብን ስኬትን መጋራት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የውድቀቱም ባለድርሻዎች ነን ማለት ይኖርብናል፡፡ እናም ሲወድቁ እንወድቃለን እንጂ እሳቸው ብቻ አይወድቁም፡፡ ሲያዘሙ ቀና ማድረግ እንጂ ጎትቶ መሬት ማስነካት በስኬታቸው ስኬታማ ነኝ ከሚል ህዝብና መንግስት አይጠበቅም፡፡ ለማንኛውም እንኳን ኖቤሉ ሀገራችን ገባ፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top