Connect with us

“ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በእርግጠኝነት ይካሄዳል” :- ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ

"ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በእርግጠኝነት ይካሄዳል" :- ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ
Photo: ETV

ዜና

“ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በእርግጠኝነት ይካሄዳል” :- ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ

ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በተቀመጠለት ጊዜ በእርግጠኝነት እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናገሩ።

ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት ሰብሳቢዋ ምርጫውን ለማከናወን ያለውን አጭር ጊዜ ታሳቢ በማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በፍጥነት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ተአማኒነትን የሚያጎድሉ ስህተቶች እንዳይኖሩም ጥንቃቄ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

ለምርጫው የሚያስፈልጉ አለም አቀፍ ግዢዎች እየተደረገ መሆኑንም ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።

የሲዳማን ክልልነትን ለመወሰን የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ለሀገር አቀፍ ምርጫው በርካታ ልምድ የተገኘበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

ምርጫ 2012 ነፃ፣ ተአማኒና ገለልተኛ እንዲሆን ቦርዱ ከቃል በላይ በተግባር ይሰራል ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን ለዚህም ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል::(ምንጭ ኢኘድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top