Connect with us

ከአማራ ክልል መንግሥት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከአማራ ክልል መንግሥት የተሰጠ የአቋም መግለጫ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ከአማራ ክልል መንግሥት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

መልካም ስነ ምግባርን በመገንባት፣ ሙስናን በመታገል ዘላቂ ሰላምንና ልማትን እናረጋግጥ!

ሙስና በአንድ ሀገር የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መረጋጋት እና ደህንነትን የሚነሳ እና ፍትህን የሚሸረሽር ዘላቂ ሰላምንና የህግ የበላይነትን የሚያናጋ ተግባር ነው። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ዋነኛ ችግራቸው ሙስና (ሌብነት) ነው::

ይህ ተግባር የአህጉሩን መከራ እና ስቃይ እያባባሰ፣ ሕዝብ እና መንግሥታትን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ ይገኛል፡፡ ስር የሰደደ እና የተስፋፋ ሙስና በተለይም በድህነት ውስጥ ለሚገኙ እና ሰፊ የስራ አጥነት ችግር ለሚታይባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ሕዝብ መንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል ከማድረግ ባለፈ ለፖለቲካ አለመረጋጋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል፡፡

የክልላችን መንግሥትም ይህን ተግባር ለማጥፋት በሚያደርገው ጥረት የተደራጁ ወንጀሎችን ማለትም የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ዘረፋን፣ ህገወጥ የሰዎችና የመድኃኒት ዝውውር እንዲሁም ኮንትሮባንድን ለመግታት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

የክልሉ የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እና በየደረጃው የተደራጁ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችንም የማኅበረሰቡን ግንዛቤ በማስፋት በሥነ ምግብር የታነጸ እና ሙስናን (ሌብነትን) መሽከም የማይችል ማኅበረሰብ ለመፍጠር ትልቅ ተልዕኮ ይዘው ተግባራቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በክልላችን ሌብነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እያስከተለ ያለው ግጭትና ብጥብጥ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ ብጥብጥ እና አለመረጋጋት በአጭር ጊዜ እንዳይገታ እንዲሁም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ጫና ቀላል እይታ የሚሰጠው አይደለም፡፡

በመሆኑም የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 2003 (እ.አ.አ) ሕዳር 30 ዓለማቀፍ የጸረሙስና ቀን ሆኖ እንዲከበር በወሰነው መሠረት በሀገር ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ “መልካም ሥነ ምግባርን በመገንባት ሙስናን በመታገል ዘላቂ ሠላምን እና ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል ስናከብር የክልላችንን ሕዝብ ሙስናን በመዋጋት በየአካባቢው የሚከሰቱ ግጭቶችን፣ አለመግባባቶችን ፣ መረን የለቀቀ ዘረኝነትን ለመግታት እና ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ሊሆን ይገባል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅበትን ሙስናን የማጋለጥ እንዲሁም ለሙስና ተባባሪ ያለመሆን ተግባርን በማጎልበት ችግር ለመፍታት በኩሉን ጥረት እንዲያደርግ የክልሉ መንግሥት ያሳስባል፡፡

መልካም ሥነ ምግባርን በመገንባት ሙስናን በመታገል ዘላቂ ሠላምን እና ልማትን እናረጋግጥ!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top