Connect with us

የህወሓት ቱማታ…የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ የሚለውን ብሂል ያስታውሰኛል!

የህወሓት ቱማታ…የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ የሚለውን ብሂል ያስታውሰኛል!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የህወሓት ቱማታ…የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ የሚለውን ብሂል ያስታውሰኛል!

የህወሓት ቱማታ…የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ የሚለውን ብሂል ያስታውሰኛል!
(ጫሊ በላይነህ)

በእውነቱ በህወሓት የሰሞኑ መስመር የሳተ አካሄድ ተናድጃለኹ፡፡ ውድ አንባቢ ሆይ ይኸ ሐተታ የዚኹ ንዴት መገለጫ አድርገህ ውሰደውና ብትፈልግ አንብበው፤ ባትፈልግ ባላየ እለፈው፡፡

ህወሓት እየከሰመ ባለው ኢህአዴግ ውስጥ አሁንም ሥልጣን እንዳለው ላስታውስህ እንጂ ለአንተ እንደአዲስ አልነግርህም፡፡ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላት መካከል 9ኙ የህወሓት ሰዎች ናቸው፡፡ ከማዕከላዊ ኮምቴውም 45 ገደማ ወኪሎች ይዘዋል፡፡ በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም በሐዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ ስለውህደት የተነሳውን አጀንዳ ያለቅሬታ ተቀብለው አጽድቀዋል፡፡ ግን የውህደቱ ሀሳብ መሬት መርገጥ ሲጀምር ደንግጠው ለተቃውሞ መራወጥ ጀመሩ፡፡

ለመቃወም ይረዱኛል ያሉትን ካርዶች ሁሉ እየመዘዙ ማብጠልጠል ሥራዬ ብለው ያዙ፡፡ የህወሓቶች የተቃውሞ አቤቱታ ብዙ ቦታ የሚረግጥ ቢሆንም ሲጠቃለል በአንድ ጉዳይ ላይ ከአቶ ለማ መገርሳ የሰሞኑ ቅሬታ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ ስሜቱ “የተገልለናል” ነው፡፡ እኛ የሌለንበት ጨረቃ አትወጣም፣ ቀኑም መሽቶ አይነጋም ዓይነት ነው፡፡

ለምን እንዲህ አልኩ?

ህወሓቶች ስለህግ የበላይነት መከበር ደጋግመው ይወተውታሉ፡፡ በእነሱ ቤት የዐብይ አስተዳደር የህግ የበላይነትን ማስከበር አልቻለም ብለው ማብጠልጠላቸው ብቻ ሳይሆን ነገሩ ሲገለበጥ “እኛ ሕግ አክባሪዎችና አስከባሪዎች ነበርን” ለማለት የሚከጅል ነው፡፡ ስለህግ የበላይነት አብዝቶ የሚናገረው ህወሓት መሆኑን ሲያስተውሉ ደግሞ ሰዎቹ አንዳች የኮሜዲ ቲያትር እየሰሩ ይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እስቲ በሞቴ፤ ህወሓት በዘመነ ሥልጣንዋ ህግና ሥርዓትን አክብራ ታውቃለችን?

ስለህግ የበላይነት በወረቀት ከተጻፈው በስተቀር ተግብራ ታውቃለችን? ተቃዋሚ የተባለን ድርጅትና ግለሰብ ሁሉ ያለምህረት ሰዶ በማሳደድ፣ በማሰር፣ በመደብደብ፣ በመግደል፣ በማስፈራራት፣ በማፈን… 27 ዓመት መጓዝ ህግ ማስከበር ነውን? ህወሓቶች ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያውያን ላይ የሰሩት ግፍ በሙሉ አፍ ለመናገርስ የሚያበቃቸው ነበርን?

ሌላው ቀርቶ ዛሬ መቀለ መሽገው “የፌዴራል ሥርዓቱ ተነካ፣ ተጣሰ” የሚሉት እነሱ ራሳቸው የፌዴራል ሥርዓቱን የት አውቀውት ይሆን? ትላንት ክልሎችን በሞግዚት ሲያስተዳድሩ እንዳልነበር ዛሬ ለእነሱ ወርቅ የሆነው የፌዴራል ሥርዓት ተነካብን ብለው ለቅሶ መቀመጣቸው ለሕዝብ ምን ፋይዳ አለው? ዛሬ የህዝብ ጥቅም ተነካ ብለው፣ የሕዝብ ተቆርቋሪ ሆነው ብቅ ያሉት ሕዝቡ የማያውቃቸው መስሏቸው ይሆን?

ደግሞ እኮ የፌዴራሊስት ሀይሎች ይባልልኛል፡፡ በምርጫ ሰሞን ከራሳቸው ያለፈ ድምጽ የማያገኙ ግለሰቦችን ሰብስቦ፣ አበል ከፍሎ ወደመቀለ በማጓጓዝ ማስጨብጨብ ራስን ከማታለል ያለፈ ምን ፋይዳ ይኖረው ይሆን?

እውን ህወሓቶች በሕዝብ ስም ጠዋት ማታ እንደሚምሉት፤ ሕዝቡን የሚወዱት ከሆነ በየሜዳው የሚረጩትን ብር አቁመው ለምን ለመቀለ ሕዝብ ንጹህ ውሃ አያቀርቡበትም? ለምን ለትግራይ ወጣቶች ሥራ አይፈጥሩበትም? ለምን ለትግራይ እናቶች የሚጠቅሙ የጤና ማዕከላትን አይገነቡበትም?…ለምን?…ለምን?

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top