Connect with us

ግልፅ ደብዳቤ ለኦቦ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር

ግልፅ ደብዳቤ ለኦቦ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ግልፅ ደብዳቤ ለኦቦ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር

ግልፅ ደብዳቤ
#ከኘሮፌሰር_ፍቅሬ_ቶሎሳ_ጂግሳ

ለኦቦ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር

የተወደዱት እና የተከበሩት ኦቦ ለማ መገርሳ፣ ከ ሁሉ አስቀድሜ የሞቀ ሰላምታዬን አቀርብሎታለሁ።

ይህን ደብዳቤ እፅፍሎት ዘንድ ያነሳሳኝ እርሶ በ የአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ ላይ ስለመደመር እና የኢህአዴግን ውህደት አስመልክተው የሰጡት ቃለምልልስ ነው። ክቡር ሆይ በ አማራና አሮሞ መካከል እንዲከስት ጠላት የፈበረክው ቅራኔ ጦዞ የዛሬ ሁለት ዐመት ኢትዮጵያን ሊበጣጥሳት በተቃረበበት ወቅት እርስዎ በአማራው አገር ተገኝተው ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ብለው አበሰሩ።

ከዛ ቀደም ለ 25 ዐመታት ስልጣን ላይ የነበሩት ሰዎች ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ተጠይፈውና ጠልተው ይኖሩ ሰለነበር እርስዎ አትዮያዊነትን ስለ አወጁ የኢትዮጵያ ህዝብ እልል ብሎ ተቀበለዎት። እርስዎ የኢትዮጵያ ርእሰብሄር አንዲሆኑም ምኞቱን እና ፍላጎቱን ገለፀ። ዘፋኞች ሳይቀሩ በዘፈን አወደሱዎት። ከህወሃት ጋራ ትግሉ ተፋፍሞ የኢሀአደግ ምርጫ ሊካሄድ ሲል እርስዎ ለጠቅላይ ሚንስቴርነት ምርጫ ብቁ ቢሆኑም ዶክተር ዐብይ ይመረጡ ዘንድ እድሎን እሳልፈው ሰጡ። ይህን በማድረጎም በዛን ጊዜ ለኢትዮያ እድገት እንጂ ለስልጣን እንደማይስገበገቡ ስለአስመሰከሩ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ ሆኑ። በድፍን ዐለም ያሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለማ ለማ እያሉ በፍቅርዎ እየነደዱ ይጮሁ ጀመር።

በአንድ ወቅት ላይ፣ እርስዎ በምግብ ተመርዘው ታመዋል ስለተባለ በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለእርስዎ ተጨንቀው ሲያለቅሱ ተስተውለዋል። ስለ እርስዎ መፈቀር እና በእርስዎ ላይ ያለው የኢትዮጵያዊነትእምነት ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ክእዚህም በላይ እርስዎ የ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የቀኝ እጅ ሆነው ኢትዮጵያን እያራመዱ ነው ተብሎ በታሰበበት ሰዐት እርስዎ በቀደም ዕለት በአሜሪካን ድምፅ ላይ በመደመር ፍልስፍና እና በ አጋር ድርጅቶቹ ውህደት አላመንኩበትም ማለትዎ የኢትዮጵያን ህዝብ አስደንግጦታል። እንዲሁም አሳዝኖታል።

በአለፉት እንድ ዐመት ውስጥ አቁዋሞ ይህ ከነበር እርስዎ ተፅእኖ ፈጣሪ እንደመሆኖ መጠን እንዴት በተቃራኒው የፓርቲዎን አባላት የመደመርን ፍልስና አይበጄነት ማሳመን ተሳኖት? የሀሳብ ልዩነት ጤነኛ እና ለእድገት መልካም ስለሆነ የሆነ ሆኖ ከልብ በመነጋገር የሚፈታ ነው። በእዚህም መሰረት ለኢትዮጵያ ደህንነት ስትሉ ከወንድምዎ ክ ዶክተር ዐብይ ጋራ ያላችሁን ልዩነት በወንድማማችነት ውይይት እንደምትፈቱት እምነቴ ነው።

ከህወሃት ጋር በተደረገው ፍልሚያ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ለውጥ የእርስዎ ሚና ጉልህ መሆኑ አይካድም። ለእዚህም ምስክሩ፣ ዶክተር ዐብይን ጨምሮ እርስዎ የሚመሩዋቸው የለውጥ ኃይሎች የለማ ቡድን መባለቸው ነው። ቡድን የሚፈጠረው ደግሞ በሰዎች መደመር ነው። ስለዚህ የመደመርን ጠቃሚነት ከ እርስዎ በላይ የሚያውቅ ሰው የለም። በኢህአደግ ውስጥ የተፈፀመውም ውህደት የእዚሁ መደመር ውጤት ነው። ሰሞኑን የብልፅግናው ፓርቲ (የኢትዮጵያ ቢባል ይሻል ነበር) በፈፀመው ውህደት ላይ እርስዎ እንደ አልተስማሙ ገልፀዋል። አኔ እንደተረዳሁት እርስዎ የሚሉት እርስዎም ሆኑ ዶክተር ዐብይ ከ ኢትዮጵያ ይልቅ የፓርቲዎን ፍላጎት ማስቀደም አንደሚገባ ነው። ስለሆነም ውህደቱን አልወደዱትም። ውድ ኦቦ ለማ መገርሳ፣ ውህደቱ ለኦሮሞ ህዝብ የሚጠቅም እንጂ በፍፁም የሚጎዳ አይደለም።

ኦሮሞዎች በብልፅግናው ፓርቲ ውስጥ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋራ በመዋሃዳቸው አብረው ይበልፅጋሉ። ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ጋራ ሆነው የመፃፍ፣ የማንበብ፣ የመናገር፣ ቋንቋቸውን እና ባህላቸውን የማስከበርና የማዳበር ነፃነታችውን ይበልጥ ይቀዳጃሉ። ተነጣጥሎ፣ ተቃቅሮና ተራርቆ ግን ይህን ሁሉ የኢኮኖሚ እና የሰብዐዊ ነፃነትን መጎናፀፍ አይቻልም። የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞውኑ በሺዎች ዘመናት አብሮነት የተዛመደ፣ የተደማመረ፣ እና የተጋመደ ነውና። አንዱ ነፃ ሳይወጣ ሌላው ሃርነቱን አይቀዳጅምና።

ክቡርነትዎ እስቲ ያስተውሉ— እነዚህ እሁን በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ የተካተቱት ሁሉ ኢትዮጵያውያን፣ ማለትም የቤንሻንጉል፣ የአፋር፣ የሱማሌ፣ የጋንቤላ፣ የሃረሪ እና የሌሎቹም ነገዶች ተወላጆች ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ይመስል በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ የአስተዳዳሪነት ስልጣን ተነፍገው የበይ ተመልካች ተደርገው፣ በገዛ ሃገራቸው አንደ ባእዳን ወደ ዳር ተገፍትረው አጋዥ የሚል የውርድት ስም ተሸክመው ዝቅ ተደርገው ይኖሩ ነበር። አሁን ግን በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ገብተው ተደራጅተው ለሃገራቸው ብልፅግና በሙሉ አእምሮአቸው፣ ልባቸውና ኅይላቸው የመሥራት ዕድል አግኝተዋል። ይህ በመሆኑም ውህደቱ እውነተኛ ፌዴራሊዝምን እና ዲሞክራሲን አንፀባርቋል። እነሱ አሁን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ነን ቢሉ ያምርባቸዋል።

ታዲይ እርስዎ ግንባር ቀድመው ኢትዮጵያዊነትን የዘመሩት እና ፋና የወጉት ሰው ሃሳብዎ ሲሳካልዎት እንዴት ቅር ይሰኛሉ? ይህ እኮ ለ ሰሚው ግራ ነው። እርስዎ ለእኛ ያልገለፁልን በመሃሉ የተፈጠረው ነገር ምን ይሆን? ነገሩ ምንም ሆነ ምን እባክዎን ስለ ሀገር አንድነት፣ ስለ ፍቅር ና ሰላም ብለው ቅሬታዎን ወደ ጎን ትተው ከወዳጅዎ እና ከትግል አጋርዎ እና ለውጡን ለማምጣት አብራችሁ ከተሰቃያችሁት ከወንድሞ ከ ዶክተር ዐብይ ጋራ በግልፅ ተወያይታችሁ ችግሩን እንድትፈቱት በኢትዮጵያ ዐምላክ ስም እለምኖታለሁ። የእርስዎ ከ ዶክተር ዐብይ ጋራ አለመስማማት የውስጥ እና የውጪ ጠላቶችን እጅግ እያስፈነጠዘ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የውስጥ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ አሰፍስፈዋል። ከውጭዎቹ ደግሞ በግብፅ የሚመሩት የዐረብ ሊግ አባላት እስየው እያሉ ጮቤ እየመቱ ነው። የሁለታችሁ ክፍተት እየሰፋ ከሄደ እነዚህ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች የጦር ኅይላቸውን አሰባስብው በክፍተቱ ውስጥ ሾልከው ኢትዮጵያን ለማጥቃት ወደ ኋላ አይሉም።

ወድ ኦቦ ለማ መገርሳ፣

የዶክተር ዐብይ ማንኛዎም የአስተዳደር፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ድል እና ቅድጅት ሁሉ የእርስዎም ጭምር ነው። በይፋ እይታወጅ እንጂ የሳቸው የሰላም የኖቤል ሽልማት የእርስዎም መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ይገነዘባል። እርስዎን ስለሚያፈቅሩዎትና ያለ እርስዎ አጋርነት እስከ አሁን የተጎናፀፉትን ሁሉ ሊጎናፀፉ እንደማይችሉ ስለ እሚያውቁ ሽልማቱን የኔ ብቻ ነው ብለው እንደማያስቡ እሙን ነው። እርስዎ እስከአሁን የሳቸው ቀኝ እጅ ነበሩና። የኢትዮጵያ ህዝብም የሚያውቀው ይህንኑ ነበር። እሁንም እሳቸው በ ወጣት ጫንቃቸው ላይ የ 28 ዐመቱን ውስብስብ መከራ ተሸክመዋል።

ኢትዮጵያን ሳላሸጋግራት እንዴት አፈገፍጋለሁ ብለው እንጂ ልባዊ ምኞታቸው በሰላም የተሞላ የምሁርነት ኑሮን ለማሳለፍ መሆኑይሰማል። እርስዎ እሳቸውን በእድሜ ለ ዐመታት እንደሚበልጡዋቸው ይነገራል። እባክዎን ለታናሽ ወንድምዎ ይራሩላቸው። ይህን ያህል ጊዜ በእናንተ መሃል አለመግባባት እንደነበር የኢዮጵያ ህዝብ መቼ አውቀ? ለካ እሳቸው መቀጣት ያለባቸውን ወንጀለኞች እንደሚገባቸው ማሰር ያልቻሉትና እርምጃ መውሰድ በሚገባቸው ጊዜ ሁሉ ያልወሰዱት አንዱም እርስዎ ከእርሳችው ጋራ እንደቀድሞው ባለመቆሞም ጭምርና ከ ገዛ ፓርቲያችው ውስጥ በገጠማቸው እክልም ኖሯል።

እሳቸው አንድ ውሳኔ ሲያስተላልፉ በፓርቲያቸው ውስጥ ያሉ አንጃዎች ውሳኔያቸውን እግር በግር እየተከታተሉ እንደሚያጨናግፉ ግልፅ የሆነው ገና አሁን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በፊት ይህን ስላልተረዳ አንዳንድ ግለሰቦች እሳችውን እንደ ደካማ መሪ እያዩ ከፍ ዝቅ እያደረጉ ሲያብጠለጥሏቸው ተደምጠዋል። እሳቸው ደግሞ ብሶታችውን እና እክላቸውን ወድ ውጭ መበተን ነገርን ማባባስ ነው ብለው ቆሽታቸው እይተቃጠለ ውስጥ ውስጡን ሲብከነከኑ ቆይተዋል ማለት ነው።

እርስዎን እና ዶክተር ዐብይን ከሞት በተቀረ ምንም አንደማይለያያችሁ ከ ወራት በፊት እርስዎ ቃል እንደመግባት ያህል ተናግረው ነበር። በሁለታችሁ መራራቅ የምስኪን ኢትዮጵያውያን ደም በከንቱ እንዳይፈስ፣ አገራችንም እንዳትበጣጠስ እና አረባዊ ጠላቶቻችን ሰርገው እንዳይገቡ እባክዎን ይህን የክብር ቃልዎን ጠብቀው ከወንድሞ ጋራ ግንባር ለ ግንባር ገጥማችሁ በግልፅ ተወያይታችሁ ልዩነታችሁን ትፈቱት ዘንድ በአፅንኦት እማፀኖታለሁ።

የእርስዎ ፓርቲ አባል ያልሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እንኳን የራሳቸውን የግል ፍላጎታቸውን ገተው ከእሳቸው ጋራ ተሰልፈዋል። እንደሚያስታውሱት በኢህአዴግ ምርጫ ጊዜ እሳቸው ሆነ ብለው ባለቀ ሰዕት ከውድድሩ ባይወጡ ኖሮ ኦሮሞው ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ባልሆኑ ነበር። እሳቸው ይህን ያደረጉት ለኢትዮጵያ ደህንነት እና አንድነት መሆኑ ስውር አይደለም። ስለሚዎድዎትና ስለሚያክብርዎት የኢትዮጵያ ህዝብ ብለው እባክዎን እንደ ብልሁ ምክትል ጠይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እርስዎም ከ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጋራ እስከመጨረሻው ይቁሙ። አብራችሁ የጀመራችሁትንም ሥራ አብራችሁ ጨርሱ። ይህንንም ለማድረግ አግዚአብሄር ይርዳችሁ።
|

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top