Connect with us

ዶ/ር ደብረጽዮን ምን እያሉን ነው ? ምስጢር አወጣለሁ!

ዶ/ር ደብረጽዮን ምን እያሉን ነው ? ምስጢር አወጣለሁ!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ዶ/ር ደብረጽዮን ምን እያሉን ነው ? ምስጢር አወጣለሁ!

ዶ/ር ደብረጽዮን ምን እያሉን ነው ? ምስጢር አወጣለሁ!

(በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን- መቐለ)

በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ባለውና ‹ህገመንግስትን እና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርአትን ማዳን›› የሚለው የምክክር መድረክ በርካታ ብሄራዊና ሃገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ታድመዉታል። ከተለያዩ ክልሎች (በተለይ ከሱማሌና ቤኒሻንጉል) የመጡት ተሳታፊዎች ልክ ሕገመንግሥቱ ሲፀድቅ እንደነበራቸው ስሜት ያለ መፈንደቅ ሲታይባቸው ነበር፡፡ ከደቡብ የመጡት ደግሞ ስሜታዊ የሚያደርግ ነገር ሲናገሩ ነበር፡፡

አንድ የቀድሞው ኢሕአዴግ አባልና የወላይታ ዩኒቨርሲቲ መምህር ‹‹ኢሕአዴግ አንድ ጊዜ ጀርባው ይጠና፤ ሌላ ጊዜ ፊቱ ይጠና እያለ አባሉንና አመራሩን ሁሉ ሲያሸማቅቅ ኖሮ፣ አሁን ፊታቸውንም ጀርባቸውንም እያስጠኑ የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው በቀረቡት ሰዎች እንዳይሆን ሆነ›› ብላለች፡፡

ከሁሉም በላይ ግን የትግራይ ክልል መንግሥት ፕሬዚዳንትና የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በመክፈቻው ላይ ያደረጉት ንግግር በአዳራሹ ውስጥ መነጋገሪያ ነበር፡፡ ወደ ስብሰባው የሚመጡ ሰዎችን የመንግሥት ቢሮክራሲ ሆን ብሎ እንዳስቀረ ገልፀው ‹ይህ የደካሞች ተግባር ነው›› ካሉ በኋላ ወዳልሆነ ነገር ከገባን እኛም ብዙ ምስጢር እናወጣለን ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

‹‹የተለየ ሃሳብ የሚፈሩ፥ በውይይት፥ በመድረክ የማያምኑ ደካሞች በዚህ መድረክ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዳይሳተፉ በተለያየ መልኩና አግባብ ጫናዎች በማካሄድ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰባቸውና ተግባራቸው አሳይተዋል። ይህ ጫናና ፀረ ዴሞክራስያዊ ተግባር መወገዝ ያለበት እና ህዝቡ በሕገ መንግስቱ የተጎናፀፈውን መብት የረገጠ አፋኝ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ መቆምና ስርአት መያዝ ይገባዋል። ሃሳብ በሃሳብ መግጠም እንጂ አስተዳደራዊ በሆኑ ጫናዎች ልዩነቶች እንዳይወጡ፥ እንዲቀበሩ እየተደረጉ ያሉ የሃሳብ ደካሞች ተግባር መቆም አለበት። አለም አንድ መንደር በሆነበት ጎረቤታሞችም እንዳይገናኙ የሚከለክሉ የአለማችን ጉደኞች ከድርጊታቸው ቢቆጠብ ይሻላቸዋል። ካልሆነ በየአካባቢው እየተከናወነ ያለው ዘርፈ ብዙ ጫና የት፥ በማን ምን እንደተፈፀመ ለህዝቡ እውነታው እንደምናወጣ ከወዲሁ ይታወቅ›› ሲሉ የተናገሩት ነገር በሻሂ ዕረፍት ወቅትና ከዚያም በኋላ በአዳራሹ ውስጥና ግቢ መነጋገሪያ ነበር፡፡

አንዳንዱ ‹በቃ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሥራውን ሊጀምር ነው የባለሥልጣናትን ጉድ ሊያወጣ ነው›› ይላል፡፡ ሌላው ደግሞ ‹‹ስለ ስመኘውን ሞት ፤ስለ ጀኔራሎቹን ግድያና ስለ ባለሥልጣናት መገደል የሚያውቁት ምስጢር አለ ማለት ነው›› ሲል፣በሌላኛው ጥግ ደግሞ ‹‹ስለ ሕዳሴ ግድብ፣ከኤርትራ ጋር ስለተደረገ ምስጢራዊ ግንኙነት፣ስለ ለማና ዐቢይ የኋላ ታሪክ ወዘተ የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን፣ እነዚህ ሰዎች እኮ 27 ዓመታት የአገሪቱን ቁልፍ ይዘው የነበሩ ናቸው›› ወዘተ እያለ ይጎረማረማል፡፡

በርግጥ ግን ዶ/ር ደብረጽዮን ምን ማለታቸው ነው?!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top