Connect with us

ጠ/ሚ/ር አብይን “ትችተዋል” የተባሉ መምህር ተፈቱ

ጠ/ሚ/ር አብይን "ትችተዋል" የተባሉ መምህር ተፈቱ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ጠ/ሚ/ር አብይን “ትችተዋል” የተባሉ መምህር ተፈቱ

ጠ/ሚ/ር አብይን “ትችተዋል” የተባሉ መምህር ተፈቱ | (ታምሩ ገዳ)

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ነው የተባለው የለውጥ አብዮት የሚዘውሩት ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ እና አስተዳደራቸውን በመጽሐፍ መልክ አብጠልጥለዋል ተብለው ለወራት ወደ እስር ቤት የተወረወሩ እንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ከእስራት ተለቀቁ።

እንደ አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል፣ የዛሬ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት፣ ፍሬው በቀለ፣ ወደ እስር ቤት የተጋዙት ባለፈው ነሐሴ 17 ቀን 2019 እኤአ ሲሆን ከሶስት ወራት የዋስትና ክልከላ በሁዋላ ባለፈው ህዳር 19 ቀን 2019 እኤአ ከእስራት ተለቀዋል።

መቀመጫውን በእንግሊዝ ፣ሎንድን ከተማ ያደረገው የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ሪፖርት መሰረት የዶ/ር አብይ አስተዳደርን “ይኮንናል” ተብሎ የተገመተው ፣ “የተጠለፈው አብዮት” ፣( The Hijacked Revolution)የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍን መምህር ፍሬው ለማሳተም ጥረት አድርገዋል የሚል ውንጀላ፣ አወዛጋቢው የጸረ ሽብር ክስ ቢቀርብባቸውም ተጠርጣሪው መምህር ከጽሑፉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው የቀደመው የአሚኒስቲ ሪፖርት ያወሳል።

መምህር ፍሬው በቀለ ምንም እንኳን ከእስራት በኋላ ቢፈቱም በምን መልኩ እንደተለቀቁ ያልገለጸው የመብት ተሟጋቹ ድርጅት”መምህር ፍሬው ቀድሞውኑ መታሰር ባልተገባቸው ነበር፣በእኛ መስፈርት መምህሩ የህሊና እስረኛ ናቸው “ሲል መታስራቸውን ኮንኗል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top