Connect with us

አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ተሰጠ

አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ተሰጠ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ተሰጠ

ፍርድ ቤቱ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ በ47 ተከሳሾች ላይ የዓቃቤ ህግን ምስክሮችን ለመስማት ትዕዛዝ ሰጠ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ የ47 ተከሳሾችን ጉዳይ ተመልክቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግን የመጀመሪያ ዙር የምስክር ቃል ለመስማት ከጥር 14 እስከ 22 ቀን 2012ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በዋለው ችሎት እስከ አሁን ያልተያዙ 10 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲሁም 3 ተከሳሾች በፖሊስ ተይዘው ባዛሬው ችሎት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ በጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው 10ሩም ሆኑ ሶስቱ ተከሳሾች በዛሬው ችሎት አለመቅረባቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ከተባሉት 3 ተከሳሾች ውስጥ ሁለቱ ከሀገር ውጭ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፥ አንደኛው ተከሳሽ ግን በቁጥጥር ስር ውሎ ለፌዴራል ፖሊስ መሰጠቱ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱ ከሀገር ውጭ ናቸው የተባሉት ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲቀርቡና ለፌዴራል ፖሊስ ተላልፎ የተሰጠው ተከሳሽም በቀጣይ ችሎት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪም በዚህ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ መጥሪያና በጋዜጣ ጥሪ ያልቀረቡ አስር ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት መወሰኑን የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top