Connect with us

ከቀጭን አምባ ማርያም እስከ ምስጢራዊው ቆጵሮስ አምባ

ከቀጭን አምባ ማርያም እስከ ምስጢራዊው ቆጵሮስ አምባ

ባህልና ታሪክ

ከቀጭን አምባ ማርያም እስከ ምስጢራዊው ቆጵሮስ አምባ

ከቀጭን አምባ ማርያም እስከ ምስጢራዊው ቆጵሮስ አምባ፤
የእመጓ ቆላ ቆይታ
****
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የእመጓ ኡራኤል ጉብኝቱ ወደ ቀጭን አምባ ማርያም እንደወሰደው ይነግረናል፡፡ ከምስጢራዊው ዋሻ እስከ ቅዱሱ ጽዋ መሰወሪያ አምባ ያደረገውን ቀጣይ ጉዞ እንዲህ ያካፍለናል፡፡
ከሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

እመጓ ተራራው ብቻ ፊደል ነው፡፡ እዚህ በዓይኔ የምመለከተውን ሸለቆ አንዳች ተአምር አነብበታለሁ፡፡ የሚነበብ ተፈጥሮ እንደ መርግ አናቴ ላይ ኾኖም ከስጋት ደስታ ሊገድለኝ ነው፡፡ ቀጭን መንገድ ይዘን ወደ ቀጭን አምባ ለመሄድ መጀመሪያ ጸበሉን ፍለጋ ወረድን፡፡

ድርሳነ ዑራኤል አሁን ስላለሁበት ስፍራ እንዲህ ይላል፡፡ “ከዚህ በኋላ ስሙ ዑራኤል የተባለው መልአክ በክንፉ የጌታችንን ደም ይዞ ወደ መንዝ ምድር ሄደ፡፡”

እንዲህ ያሉ ድንቅ መንፈሳዊ ታሪኮች የእመጓን ታሪክ ከፍ አድርገውታል፡፡ ከተፈጥሮው መስህብ ከታሪኩ መግዘፍ በላይ የምስጢራዊ ስፍራ ማዕከል ሆናለች፡፡ አንድ ስፍራ በብዙ የምትገለጥ ቦታ፡፡

ጸበሉ ጋር ደረስን፡፡ ግዙፍ ቋጥኝ ከደመናው ጋር የተጣበ መስሏል፡፡ እግሩ ስር ጠበሉ ይፈልቃል፡፡ ቆመን በሁሉ ተመሰጥን፡፡ የእመጓ ቆላ ሸለቆው ውስጥ ዝቅተኛ ከሚባለው ስፍራ ነኝ፡፡ ይሞቃል፡፡

ወደ ዋሻው ጉዞአችንን ቀጠልን፡፡ ከጸበሉ ዋሻው ያለው መንገድ ለምን መጣሁ የሚያስብል የአበሳ ጎዳና ነው፡፡ ያም ቢኾን ገደል እንደሜዳ ዘር ዘርቶ የሚኖር ብርቱ ገበሬ ሰብሉን ሲያነሳ ደርሰናል፡፡ እዚህም እዚያም የሕይወት ትዕይንት፣ ጥሮ ግሮ የማደር እውነት ይታያል፡፡

ዋሻው ጋር ደረስን፡፡ ሰፊ ነው፡፡ አናቱ ግዙፍ አለት ተሸክሟል፡፡ በድንጋይ ተቀጥሯል፡፡ በራፍ የለውም፡፡ ወደ ውስጡ ገባን፡፡ ጣሪያው ጥቁር ነው፡፡ ውስጡ ትንሽ ሲጠጉ ከፍታው እየቀነሰ ሄዶ ያስጎነብሳል፡፡ ርቀቱን የደፈረው የለም፡፡ የሞከረው ዱቄት መሳይ አፈር ያለበት ድረስ መሄድ የቻለ ጀግና ብቻ ነበር፡፡ ሩቅ ያወጣል ብለው ያምናሉ፡፡ ሲያልፍም ምስጢራዊ ዋሻ መሆኑን ሰማሁ፡፡ ምስጢሩን ለመድረስ እውቀትም ብቃትም ይፈልጋል፡፡ ወደ ቀጭን አምባ ዳገቱን ይዘን ተጓዝን፡፡

ሊቀ ካህናት ኢሳያስ የመንዝ ማማ ቤተ ክህነት የስራ ሃላፊ ናቸው፡፡ ፍለጋዬን አፋልገው ዳገት ወጥተው ቁልቁለት ወርደው አብረውኝ ይደክማሉ፡፡ ፈታኟን ዳገት ስንጨርስ ረዣዥም ጥድ የከበባት ደብር ታየች፡፡ ጉልላቷ፤

ቀጭን አምባ ማርያም ቀደምት ናት፡፡ ትንሷ ቤተ ክርስቲያን እጅግ ረዥም ጥድ ተጠግታ ቆማለች፡፡ ገዳም ስለሆነች መነኮሳት አሉ፡፡ ሰበካዋ ግን በእመጓ ኡራኤል ስር ነው፡፡ ጸበሏ ፈዋሽ በመሆኑ ጠበልተኛው ብዙ ነበር፡፡ ያለችበት አካባቢ መልከዓ ምድር ዓይን ያፈዛል፡፡ ልብ ይወስዳል፡፡

የሦስት ቀን ውሎ የምተርክ የማይመስለው የዋህ በየእርምጃው ያገኘኋቸው መስህቦች ይመስሉታል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ወደ ቆጵሮስ አናት ጉዞ ጀመርኩ፡፡ ቆጵሮስ ምስጢራዊው አምባ ነው፡፡
ድርሳነ ዑራኤል ቆጵሮስን እንዲህ ይላታል፡፡

“ያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል በዚያች በቆጵሮስ ገዳም ውስጥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ደም ረጨ” ድርሳነ ዑራኤል ዘ መስከረም፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top