Connect with us

በማዕከላዊ ጎንደር የደብረሲና ማርያም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ተከበረ

በማዕከላዊ ጎንደር የደብረሲና ማርያም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ተከበረ

ባህልና ታሪክ

በማዕከላዊ ጎንደር የደብረሲና ማርያም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ተከበረ

በማዕከላዊ ጎንደር የደብረሲና ማርያም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ተከበረ
(በድሬቲዩብ ሪፖርተር- ጎንደር)

በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ ጎርጎራ ከተማ የሚገኘው የደብረሲና ማርያም አንድነት ገዳም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው ሲምፖዚየም ተካሄደ።

ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደው ሲምፖዚያም ላይ የተገኙት ዶ/ር አሥራት አፀደወይን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝደንት እንዳሉት የደንቢያ ወረዳ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምስረታ መሠረት እንደነበር አስታውሰዋል። ዩኒቨርሲቲው በ1947 ዓ.ም በአካባቢ የወባ ወረርሽኝ በአካባቢው ያስከተለውን ከባድ ጉዳት ለመቅረፍና የህዝቡን ጤና ለመጠበቅ በንጉሰ ነገስቱ ትዕዛዝ የጎንደር ጤና አጠባበቅ ማሰልጠኛ ተቋም በሚል መመሥረቱን አስታውሰዋል። እዚህ አካባቢ ዩኒቨርሲቲው የሚያደርገው ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ቢኖሩም ከምንፈልገው አንፃር ገና ምንም እንዳልሰራን ይሰማናል ብለዋል።አያይዘውም የደብረሲና ማርያም ገዳም 700ኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

አቶ መላኩ አላምረው የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ በበኩላቸው በቅርስ ሐብት በተለይ ጎርጎራና አካባቢው ከዓለም ልዩ እንደሚያደርገው መስክረዋል። በቱሪዝም ዘርፍ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችም ማለትም መስህብ ዋናው ሲሆን በዚህ ረገድ ሰፋ ያለ ሐብት መኖሩን ጠቁመዋል። ሁለተኛው መዳረሻ ማለትም መንገድና የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች ሲሆኑ የመጨረሻው መቆያ ማለትም ሆቴሎች፣ሎጆችና የመሳሰሉ ናቸው ብለዋል። በእነዚህ ረገድ ድክመት መኖሩን ተናግረዋል።

 

መንግስት በዋንኛነት ዘርፉን የማሳደግ ሀላፊነት ቢኖርበትም የህዝቡ ተሳትፎ ካልታከለበት ውጤታማ እንደማይሆን አስረድተዋል።
በጎርጎራ የተካሄደው ሲምፖዚየም በዛሬው ውሎው በዋንኛነት ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውነው ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በኘሮፌሰር መርሻ ጫኔ የቀረበ ሲሆን በጎርጎራ እና አካባቢው ላይ የሚገኘውን የቱሪዝም አቅም እና የቱሪዝም ተግዳሮቶች እንዲሁም የደብረሲና ማርያም የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በትላንትናው ዕለት በጎርጎራ አካባቢ የሚገኙ ጥንታዊ ገዳማት የሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታ የመስክ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን በጉብኝቱ ኘሮግራም ላይ በዋንኛነት የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ገዳማቱ በዋንኛነት ለዘመናት ያቆዩዋቸው ቅርሶችን ለመጠበቅና ለመንከባከብ የሚያስችል አቅም ማጣታቸውንና ቅርሶቹ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ በገሊላ ኢየሱስ አቡነ ዘካርያስ ገዳም ከ20 ዓመታት በላይ በአንድ ቤት ታሽጎባቸው እንደሚገኙ ተጠቁሟል። በማንዳባ ገዳም የሚገኙ ቅርሶች ደግሞ መሬት ቆፍሮ በመደበቅ ለመጠበቅ እየሞከሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።ጥንታዊው የአፄ ሱሰንዮስ ቤተመንግሥት (የአፄ ፋሲል አባት) ቤተመንግሥት ከፈራረሰ ዓመታትን ቢቆጥርም ተገቢውን ጥገና በማድረግ የቱሪዝም መስህብ ማድረግ እንዳልተቻለ ተነግሯል።በተጨማሪም በአካባቢው ደረጃውን የጠበቀ የትራንስፖርትና ሆቴል መሰረተ ልማት አለመኖር በቱሪዝም ዘርፍ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩ በገዳማት አባቶች ተናግረዋል።


ቅርሶቹ በሙዝየም ደረጃ አለመቀመጣቸው በአካባቢው የቱሪዝም ገቢ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ጫና እያሳረፈ ነው ተብሏል።
ይህ ሲምፖዚየም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝም ዘርፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት አንድ አካል ነው።
ህዳር 21 ቀን 2012 ዐዓ.ም በጎንደር ጎርጎራ ከተማ የሚገኘው የደብረሲና ማርያም አንድነት ገዳም 700ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተከብሯል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top