Connect with us

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ

የአቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከወሰን ማስከበር ነፃ የሆነውን የመንገዱን ክፍል የሰብ ቤዝና የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጀምሯል፡፡

ይሁን እንጂ በርካታ የመሰረተ ልማት መስመሮችና የግለሰብ ቤቶች ከመንገዱ የወሰን ክልል ውስጥ በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ባለመነሳታቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን እንቅፋት ሆነዋል፡፡

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ

የአቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከወሰን ማስከበር ነፃ የሆነውን የመንገዱን ክፍል የሰብ ቤዝና የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጀምሯል፡፡

 

አሁን ላይ በመንገድ ፕሮጀክቱ ውስጥ ከሚገኙት ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎች መካከል 85 የቴሌ መስመሮች፣ የኔትወርክ ሳጥኖች፣ 157 የሚሆኑ የመብራት ሀይል ምሰሶዎች እና በቁጥር 15 የሚጠጉ ቤቶች ይገኙበታል፡፡ በእነዚህ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎች የተነሳም 1 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የሚሆነው የፕሮጀክቱ ክፍል ላይ ምንም አይነት የግንባታ ስራ አልተጀመረም፡፡

አሁን ላይ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት የመንገድ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠናቆ የህብረተሰቡን የመንገድ ጥያቄ በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ 5 ነጥብ 3 ኪ.ሜ ርዝመት እና 25 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል፡፡

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ – ቱሉ ዲምቱ መንገድ ለረጅም ዓመታት በማገልገሉ የተነሳ የተጎዳ፣ ስፋቱም ከሰባት ሜትር ያልበለጠ በመሆኑ ጠባብና ምቹ የእግረኛ መንገድም የሌለው ነበር፡፡ መንገዱ በአዲስ መልክ መገንባቱ የአካባቢውን ገፅታ ከመቀየሩም ባለፈ ለመዲናዋ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይኖረዋል፡፡

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም የከተማዋ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግንባታ ስራው በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡(ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top