Connect with us

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ!
Photo: Facebook

ማህበራዊ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ!

(ጋዜጣዊ መግለጫው እነሆ)

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን የትምህርት ዘመን መጠነ ሰፊ ዝግጅቶችን በማድረግ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡ በትምህርት ዓመቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ካሉት ዋና ዋና ለውጦች መካከል ዩኒቨርስቲዎችን በተልዕኮ የመለየትና ለሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች አጠቃላይ እውቀት ፣ ክህሎትና ስነምግባር ክፍተቶችን የሚሞሉ የተለያዩ ይዘቶች ያሏቸው አዳዲስ ኮርሶች ይገኙበታል፡፡

እነዚህንም ለውጦች እውን ለማድረግና ዩኒቨርስቲዎችን ሰላማዊ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የልህቀት ማዕከላት ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ተካሂደው የትምህርት ዘመኑ ተጀምሯል፡፡

በዚህ መሰረት ዩኒቨርስቲዎቻችን ከመስከረም አጋማሽ ጀምረው ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የመማር ማስተማር ስራውም ከቀደሙት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ እያካሄዱ ባለበት ጥቅምት 29 ቀን 2012 ዓ.ም በአንድ ዩኒቨርስቲ ያጋጠመ ጸብ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በመዛመቱ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰኑት ዩኒቨርስቲዎቻችን በተለያዩ ደረጃዎች የሚገለፅ የመማር ማስተማር መስተጓጎል አጋጥሞ ነበር፡፡

በዚህ ሂደት ዩኒቨርስቲዎችን የሁከት ማዕከል ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት አጋጥመው የነበሩ አለመረጋጋቶችና ሲቆራረጡ የቆዩ የመማር ማስተማር ተግባራት ወደ መደበኛና ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በእነኚህ ቀናት ተማሪዎችን በማወያየት፣ በመምከር እና በመደገፍ ዩኒቨርስቲዎቻችን ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ላደረጋችሁ የአከባቢ መስተዳድር አካላት፣ የፌደራልና

የክልል የፀጥታ መዋቅር አካላት፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በቀጣይ ጊዚያትም ዩኒቨርስቲዎቻችን ለአገራችን ሰላምና

ብልፅግና መሰረት የሚጣልባቸው ማዕከላት እንዲሆኑ በቀጣይም የሁላችሁንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ስለሆነ ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን፡፤

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪዎች ተረጋግተው እንዳይማሩ “የትውልድ አከባቢችሁ ባሉ ዪኒቨርስቲዎች ቅበላ ታገኛላችሁ” በማለት የሚቀሰቅሱና መዝግበውም ተማሪዎችን ከግቢ ይዘው ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ተረድተናል፡፡ እንደዚሁም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመማር ማስተማሩ ሒደት እንደሚቋረጥ አሳውቋል በሚል የተሳሳተ መረጃ ተማሪዎችን በማወናበድ እና የመማር ማስተማሩ ተግባር እንዲስተጓጎል የሚያደርጉ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህን አካላት የመለየትና ተገቢውን የእርምት እርምጃ የመውሰድ ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ተማሪዎች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት በዚህ ተግባር ተሳትፈው አሉታዊና እና አፍራሽ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነው ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የበኩላችሁን እንድትወጡ እናስገነዝባለን፡፡

መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና በየደረጃው ያላችሁ የዩኒቨርስቲ አመራር አካላት ሁሉም ፈፃሚና መሪ በመደበኛ ስራው ላይ መሆኑን እና ግዴታውን እየተወጣ ስለመሆኑ ክትትል በማድረግ ተገቢውን አመራር እንድትሰጡ በዚህ አጋጣሚ እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም ዩኒቨርስቲዎቻችን የብቁ ምሩቃን ማፍሪያ እና የልማታችን አንድ አካል መሆናቸውን እንድናረጋግጥ፤ እያልን ተቋሞቻችንን ላልተገባ ዓላማ ለመጠቀም እንቅስቃሴ የሚያደርጉት አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top