Connect with us

በነዳጅ ማስቀመጫ ታንከር ውስጥ ደብቆ 34 ሽጉጥ ያስገባ ተጠርጣሪ ተያዘ

በነዳጅ ማስቀመጫ ታንከር ውስጥ ደብቆ 34 ሽጉጥ ያስገባ ተጠርጣሪ ተያዘ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በነዳጅ ማስቀመጫ ታንከር ውስጥ ደብቆ 34 ሽጉጥ ያስገባ ተጠርጣሪ ተያዘ

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ቁጥጥር በተሸከርካሪ የነዳጅ ማስቀመጫ ታንከር ውስጥ ደብቆ ወደ አ/አበባ የገባ 34 ሽጉጦች ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

መነሻውን ሀረር ከተማ ያደረገው ኮድ 3-63951 ኦ/ሮ የሆነ ሀይሩፍ ሚኒ ባስ ተሸከርካሪ በተሸከርካሪው የነዳጅ ማጠራቀሚያ ስልቫቲዮ ውስጥ ለመደበቅ እንዲያመቸው በብረት ክፍል በጥንቃቄ ሰርተውለት ሽጉጦችን በላስቲክና በፕላስተር በማሸግ አ/አበባ ከተማ ውስጥ ካስገቡ በኋላ ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም ተሸከርካረው ሲፈተሸ 33 እስታር ሽጉጥ እና አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ ከነተጠርጣሪው ሊያዝ መቻሉን በአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች መርማሪ ዋ/ሳጅን ታረቀኝ ወዳጆ ተናግረዋል፡፡

ሽጉጦችን በተሸከርካሪው የውስጥ አካል ላይ በድብቅ ለማሳለፍ ታስቦበት የተሰራ ህገ-ወጥ ተግባር ቢሆንም ከ4 ሰዓት በላይ በባለሙያ ጭምር ታግዞ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ፍተሻ ሽጉጦቹ የተገኙ መሆኑን መርማሪው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች ምንም እንኳን ህገ-ወጥ ተግባራቸውን በስውርና በጨለማ ተጨንቀውና ተጠበው ቢፈፅሙም የፖሊስ አይንና ጆሮ የሆነው መላው ሠላም ወዳዱ ህብረተሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በዜጎች ላይ ሊደርስ የታሰበን የወንጀል ድርጊት እያከሸፈ ይገኛል ካሉ በኋላ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን የሥራ ትስስር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

መረጃዉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነዉ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top