Connect with us

የዕለት ጠብ ጥንዶቹን በሞት ለያየ

የዕለት ጠብ ጥንዶቹን በሞት ለያየ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የዕለት ጠብ ጥንዶቹን በሞት ለያየ

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጊዜዊ አለመግባባት ጨካኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ የትዳር አጋሩን በሆዷ ከያዘችው ጽንስ ጋር የገደለው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በ16 አመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ::

ተከሳሽ ልጃአለም ታደሰ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ መስከረም 21 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ክልል ልዩ ቦታው ሀያት ቁጥር 2 ኮንዶሚኒየም በሚኖሩበት የቤት ቁጥር ውስጥ ህጋዊ ባለቤቱ ከሆነችው ሟች ጋር በተፈጠረ ጊዜዊ ጸብ ሲገፈታተሩ ሟችም ስትያያዘው ተከሳሽ በትቦ ብረት ጭንቅላቷን በመምታት አልጋ ላይ ስትወድቅ በድጋሜ ባደረሰባት ጉዳት ባስከተለው የደም መፍሰስ ምክንያት እሷ እና በሆዷ ውስጥ የነበረ ከ3-4 ወራት እድሜ ያለው ጽንስም ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ በመሆኑ ጨካኝነትንና አደገኛነትን በሚያሳይ ሁኔታ በፈጸመው ከባድ ግድያ ወንጀል መከሰሱን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

የልዩ ልዩ ወንጅል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በፖሊስ የምርምራ መዝገብ መሰረት የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች ከክስ መዝገቡ ጋር በመያዝ በማስረጃነት ለፍርድ ቤት አቅርቧል::

ተከሳሽ ማንነቱ በችሎት ተረጋግጦ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን ፈፅሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ በማለት በቤት ውስጥ ቡና እየተፈላ ሟች ህፃን ልጃቸውን ሲኒ ሰበረች በሚል ስትመታት ለምን ትመቻታለች በሚል በድጋሜ ስትመታት እና ህፃኗ ስትጎዳ በሟች ድርጊት ስሜት ዉስጥ በመግባቱ ድርጊቱን መፈፀሙን ለፍርድ ቤቱ ቃሉን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹን በተከሰሰበት ወንጀል 539/1/ሀ ስር ጥፋተኛ ነህ ተብሏል::

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሹ ሪከርድ ያሌለበት፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በማቅለያ በመቀበል ህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ16 አመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል::

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top