Connect with us

የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ረቂቅ ሰነድ ለውይይት ቀረበ

የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ረቂቅ ሰነድ ለውይይት ቀረበ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ረቂቅ ሰነድ ለውይይት ቀረበ

የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ረቂቅ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ አዲስ አበባ ላይ እየመከሩበት ነው።

የአስተሳሰብ ፍልስፍና ሰነዱ በፖሊስና በኅብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን የተዛባ ግንኙነት የሚያስተካክል እንደሆነ ተነግሯል።

ከሕዝብ ጎን የሚቆም ገለልተኛ የፖሊስ ተቋም መገንባት የሚያስችሉ የፖሊስ ማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

ከስራዎቹ መካከል የፖሊስ ተቋምና አገልግሎትን በአዲስ መልክ በማደራጀት ፖሊስ የሚመራበት የአስተሳሰብ ፍልስፍና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ተጠቃሽ ነው።

ዛሬ በቀረበው የፖሊስ የአስተሳሰብ ፍልስፍና /ዶክትሪን/ የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ ውይይት ላይ የተገኙት የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የተቋሙን የአስተሳሰብ ፍልስፍና ከኢትዮጵያዊ እሴቶችና ከዴሞክራሲ መርሆች ጋር አስተሳስሮ መቅረጽ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የፖሊስ የአስተሳሰብ ፍልስፍና ዋነኛ ዓላማ በዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት የፖሊስን ከፍተኛ ቦታ አጉልቶ ማውጣት መሆኑን አንስተዋል።

ይህ የአስተሳሰብ ፍልስፍና በኅብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ለዘመናት ተዛብቶ የቆየውን ግንኙነት የሚያቀና ነው ብለዋል ወይዘሮ ሙፈሪያት።

“የዴሞክራሲ መርሆዎችን ተከትለን የምንገነባው ተቋምና አገልግሎት በሕግና በሕግ የሚመራ፣ ከአድልዎ የራቀና የኢትዮጵያን ሕዝብ በቅንነት የሚያገለግል ነው” ብለዋል።

የሕግ፣ የፖሊሲና ስትራቴጂ፣ የአደረጃጀት፣ የምልመላና ስልጠና፣ የሎጂስቲክስና የትጥቅ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀም በፖሊስ ተቋምና አገልግሎት ላይ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል በውይይቱ ተነስቷል።

በውይይቱ እንዲሳተፉ ከ300 በላይ የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥሪ የተደረገ ቢሆንም የታደሙት ግን ከግማሽ በታች የሚሆኑት ናቸው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top