Connect with us

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት ማደግን ተከትሎ የህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ሆኖም እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት መሸከም የሚችል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በዚያው መጠን ባለመዘርጋቱ እንዲሁም ያለውንም በማርጀቱ ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ እንዲሁም የኃይል ብክነት ሲያጋጥም ይስተዋላል፡፡ይህም በከተማዋ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ህብረተሰብ እና በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም አንዱ የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ነው፡

የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት እየተከናወነ የሚገኘው ፓወር ቻይና ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኦፍ ቻይና በተሰኘ የቻይና ኮትራክተር ሲሆን፤ አማካሪው ደግሞ የተቋሙ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ሎካላይዜሽን የስራ ክፍል ነው፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ162 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ ሲሆን፤ የቻይና የመንግስት 85 ከመቶ እና የኢትዮጵያ መንግስት 15 በመቶ ይሸፍኑታል፡፡

የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የሲቪል ግንባታ ሥራ የተጀመረው ጥቅምት 2009 ዓ.ም የኮንትራክተር ግዢ እና የፕሮጀክት አማካሪ ቅጥር ከተፈፀመ በኋላ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ኢንጂነሪንግ፣ የዕቃ ምርት እና አቅርቦት፣ የግንባታ ሥራ፣ ኢንስታሌሽን ሥራዎች ሙሉ ለሙሉ የሚሰራው በኮንትራክተሩ ሲሆን፤ 14 አገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶችን በማሳተፍ ለ632 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ፕሮጀክቱ የመካከለኛ ቮልቴጅ ዋና መስመር ግንባታ እና ጥገና ሥራ፣ ያረጁ ነባር መካከለኛ ቮልቴጅ መስመር የመቀየር ስራ፣የዝቅተኛ ቮልቴጅ መስመር ዝርጋታና የትራንስፎርመር ተከላ እና የአውቶሜሽን ሲስተም ዝርጋታ ስራዎች አሉት፡፡

ኮንትራክተሩ ወደ ስራ የገባው 146 ኪ.ሜ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ ኬብል (UG) 77.84 ኪ.ሜ ድርብ (double circuit) እና 68.17 ኪ.ሜ ነጠላ (sigle circuit)፣ 492.5 ኪ.ሜ የአየር ላይ 15 ኬ.ቪ መስመር፣ 25.86 ኪ.ሜ ድርብ (double circuit)፣ 466.69 ኪ.ሜ ነጠላ (sigle circuit)፣ 72 የስዊቺንግ ስቴሽን ተከላ ስራ፣ 461 (400 ኦቨር-ሄድ እና 61 ኮምፓክት የትራንስፎርመር ተከላ፣ 400 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ስራ እና የዲስትሪቢዩሽን አውቶሜሽን ሲስተም ዝርጋታ ስራዎች ለማከናወን ከተስማማ በኋላ ነው፡፡

ኮንተራክተሩ በገባው ውል መሰረት በመካከለኛ ቮልቴጅ ዋና መስመር ግንባታ እና ጥገና የስራ ዘርፍ በመሬት ዉስጥ የሚቀበሩ አዲስ መስመርና ነባሩን በአዲስ መልክ መልሶ የመገንባት፤ የአየር ላይ የመካከለኛ ቮልቴጅ ዋና መስመር ግንባታ ሥራ፣ ስዊቺንግ ስቴሽኖች ተከላ ስራዎች በማከናወን ከፕሮጀክቱ ይዘት አንጻር 98.3% አጠናቋል፡፡

ነባርና ያረጁ የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር መቀየር፣ ከስዊቺንግ ስቴሽን የሚወጣ የአየር ላይ መካከለኛ ወጪ መስመር ዝርጋታ እና ከነባሩ ወደ አዲስ መስመር ኃይል የማዘዋወር ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በዝቅተኛ ቮልቴጅ መስመር ዝርጋታ እና የትራንስፎርመር ተከላ የስራ ዘርፍ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ፣ትራንስፎርመር ተከላ፣ የኮምፓክት ሰብስቴሽን ተከላ፣ ምሰሶ ላይ ተሰቃይ (ፖል ማውንትድ) ስራ በማከናወን 76.9% ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

በአውቶሜሽን ሲስተም ዝርጋታ የጥቁር አንበሳ፣ አዲስ ኢስት፣ አዲስ ሴንተር፣ ወረገኑን እና ንፋስ ስልክ ሰብስቴሽኖችን የሚያገናኝ የኦፕቲክ ፋይበር ኬብል መስመር ዝርጋታ ስራም ተጠናቋል፡፡

ቀሪው የአውቶሜሽን ስራ በአዲስ በመጀመር ላይ ባለው የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ውስጥ ተጠቃሎ እንዲከናወን በመወሰኑ ተጨማሪ 225 ኪ.ሜ. የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 96.05% የደረሰ ሲሆን፤ በአውቶሜሽን ስራው ይዘት ምትክ እንዲሰራ የተወሰነውን 225 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር የመልሶ ግንባታ ስራ፣ የ11 ስዊቺንግ ስቴሽኖች ተከላ እና የ39 ኪ.ሜ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ የመለዋወጫ ኬብል የማቅረብ ስራ በቀጣይነት ለማሰራት ስምምነት ላይ ተደርሶ ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር አቅም ይፈጥራል፤ በአንድ አካባቢ ለሚገኝ ህብረተሰብ ክፍሎች ከተለያዩ ሰብስቴሽኖች ኃይል ማግኘት እንዲችል በማድረግ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ይቀንሳል፤ የህብረተሰቡን የኃይል አጠቃቀም በማሻሻል ቴክኒካልና ቴክኒካል ያልሆኑ የኃይል ብክነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

በተጨማሪም የከተማይቱን የኃይል አቅርቦት በማሻሻል አስተማማኝነትና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፤ ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፤ በአንድ አካባቢ የጥገና ስራ ለመስራትም ሆነ በሌላ ተያያዥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ሲያስፈልግ የተፈለገውን አካባቢ ብቻ ለይቶ ለማቋረጥ ያስችላል፡፡ ፕሮጀክቱ ብልሽት ሲያጋጥም የብልሽቱን ቦታ በቀላሉና በአፋጣኝ ለመለየት ያስችላል፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ መስመሮች መቆጣጠሪያ ጣቢያ በመታገዝ በከተማዋ የሚገኙትን የኃይል ማሰራጫ መስመሮች በዘመናዊ መንገድ መቆጣጠር መቻል እና በጥሪ ማዕከል አማካኝነት ከደንበኞች የሚመጣ የብልሽትም ሆነ ተያያዥ ጥሪዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እና ሌሎች ተያያዥ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳዎችን ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡(ምንጭ፡-የኤሌክትሪክ አገልግሎት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top