Connect with us

ቆሞ ቀሩ የሀገር ሐብት

ቆሞ ቀሩ የሀገር ሐብት
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ቆሞ ቀሩ የሀገር ሐብት

በኮርፖሬሽኑ የአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሐራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት እንደሌሎቹ ፕሮጀክቶች በብድርና ዕርዳታ ተገንብቶ 99 በመቶ የተጠናቀቀው ከሶስት ወራት በፊት ነው፡፡ ግን ባቡሩ የኤሌክትሪክ በመሆኑ መልኩን አሳምሮ ቁጭ ለማለት ተገድዷል፡፡ ለምን ሲባል ኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት አልቻለም፡፡

የኤሌክትሪክ አገልግሎት አንድ ጊዜ ክፍያ አልተፈጸመልኝም፣ ሌላ ጊዜ ቢጀመርም ሥራው ከ18 ወራት በላይ ይወስዳል የሚሉ ሰበቦችን በመደርደር የሀገር ሐብትን ቆሞ እንዲቀር ፈርዶበታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጀመር አብሮ መታሰብ የነበረበት ይኸ ሥራ ለምን በወቅቱ ሳይከናወን እንደቀረ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ መንግሥት ከዚህ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ስራቸውን በአግባቡ መወጣት ያልቻሉ አመራሮችና ባለሙያዎችን ዝም ማለቱም ግራ ያጋባል፡፡

የሆነስ ሆነና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ቻይናን በጎበኙበት ወቅት ከቻይናው ኤስ ጂ ሲ ሲ ኩባንያ ጋር ለኃይል ማሠራጫና ማከፋፈያ መሥመር ዝርጋታ በሚል የፈረሙት የአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ስምምነት ከምን ደርሶ ይሆን?

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top